Artwork for የዓለም ዜና
News

የዓለም ዜና

DW

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።

  • 100 episodes
  • Updated Yesterday

Episodes100

  • Yesterday · 12 min

    የሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    የሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ-ዜና በራያ አላማጣ ግንባር ወታደራዊ ፍጥጫ እና የጦርነት ዝግጅት ማየሉን ነዋሪዎች ገለጹ። በአካባቢው ፣ ቤት ለቤት ዝርፊያ መስፋፋቱን የትራንስፖርትና የባንክ አገልግሎት በመስተጓጐሉ ደንበኞች ለተጨማሪ ክፍያ መዳረጋቸውንም ተናግረዋል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጦርነት ሸሽተው ከትግራይ ክልል ወደ ሱዳን እየገቡ ነው ሲል ኤ ኤፍ ፒ ዘገበ። ከመካከላቸው ቁስለኛ ተዋጊዎች ይገኙበታል የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚካሄደውን ጦርነት ከፍጻሜ ለማድረስ ዛሬ ሰኞ ድርድር ይጀመራል ሲሉ ቴህራን ደግሞ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ድርድር እያካሄድኩ አይደለም ብላለች

  • Sunday · 8 min

    የሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

    በመከላከያ ሠራዊትና በትግራይ የጸጥታ ኃይሎች መካከል ሸረሪና በተባለ ቦታ የተጀመረው ውጊያ መቆሙን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ። እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ፈጸመችው በተባለ የአየር ጥቃት 15 ፍልስጤማውያን ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ጦርነቱን ለማስቆም በአፋጣኝ ስምምነት ላይ ከተደረሰ ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ላለመሰንዘር መስማማታቸውን ገለጹ። በኢንዶኔዥያ በአንዲት ጀልባ በደረሰ የእሳት አደጋ 5 ተሳፋሪዎች ሞተው 41 የደረሱበት አለመታወቁን የሐገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።

  • Sunday · 10 min

    የሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    የዛሬው የዓለም ዜና ፤በትግራይ አዲስ ጦርነት መከፈቱን የትግራይ ቴሌቪዥን መዘገቡን፣በሲውታ፤ ስፔን እና ሞሮኮ የድንበር በተከሰተው የስደተኞች ቀውስ የሟቾች ቁጥር 67መድረሱን፣በስፔኗ ሲኡታ ግዛት የሚፈልሱ ስደተኞችን በተመለከተ ውይይት እንዲደረግ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ጥሪ ማቅረባቸውን፣ሁቲዎች የሳውዲ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች የጉዞ መስመር እንዲቀይሩ ማድረጋቸውን፣እስራኤል በፈፀመችው ጥቃት በጋዛ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘኖችን መውደማቸው መገለፁን እንዲሁም ኢራን አሜሪካን እንዳያግዙ የአካባቢውን መንግስታትን ማስጠንቀቋን አካቷል።

  • Saturday · 10 min

    የሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    የዛሬው የዓለም ዜና ፤በትግራይ አዲስ ጦርነት መከፈቱን የትግራይ ቴሌቪዥን መዘገቡን፣በሲውታ፤ ስፔን እና ሞሮኮ የድንበር በተከሰተው የስደተኞች ቀውስ የሟቾች ቁጥር 67መድረሱን፣በስፔኗ ሲኡታ ግዛት የሚፈልሱ ስደተኞችን በተመለከተ ውይይት እንዲደረግ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ጥሪ ማቅረባቸውን፣ሁቲዎች የሳውዲ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች የጉዞ መስመር እንዲቀይሩ ማድረጋቸውን፣እስራኤል በፈፀመችው ጥቃት በጋዛ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘኖችን መውደማቸው መገለፁን እንዲሁም ኢራን አሜሪካን እንዳያግዙ የአካባቢውን መንግስታትን ማስጠንቀቋን አካቷል።

  • Friday · 11 min

    የሐምሌ 24 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    -የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ባለሥልጣን «የይዘት ግዴታዎችን ተላልፈዋል» ላላቸዉ ለሁለት የሐገር ዉስጥ ማሰራጪያ ጣቢያዎች «የመጨረሻ« ያለዉን የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። ማስጠንቀቂያዉ የተሰጣቸዉ አሐዱ ኤፍ ኤም 94.3ና አርትስ ቴሌቪዥን ጣቢዎችን ባለሥልጣኑ «ያልተረጋገጠ፣ ሚዛናዊ ያልሆነና የሕዝብ ጥቅም የሚጎዱ» ያላቸዉን መረጃዎች አሰራጭተዋል በማለት ወቅሷልም።-ሶማሊያ ዉስጥ ለሰፈረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት ወታደሮች ያዋጡ ሐገራት መሪዎች ዛሬ ሲነጋገሩ ዋሉ።--ከ60 ሺሕ የሚበልጡ ስደተኞች ባጭር ጊዜ ዉስጥ የስጳኝን ግዛት ሴኡታን ማጥለቅለቃቸዉ ለስጳኝና ለሞሮኮ አስደንጭ፣ ለተቀሩት የአዉሮጳ ሐገራት አሳሳቢ ሆኗል።

  • Thursday · 10 min

    የሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

    • የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ ከማላዊ ፖሊስና ከኢንተርፖል ጋር በመተባበር በኢትዮጵያዉን ወጣቶች ላይ «ከባድ ኢሰብአዊ ድርጊት ሲፈጽም ነበር» ያለዉን ተጠርጣሪ መያዙን አስታወቀ። • በሱዳን ሰሜን ኮርዶፋን ግዛት በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ዘጠኝ ሰቪሎች መገደላቸውን የሕክምና ምንጮች ገለጹ። • በግብፅ ዳሚየታ ወደብ ላይ የደረሰው ቃጠሎ የድሮን ጥቃትን ተከትሎ የተነሳ መሆኑን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዐስታወቀ። • ሩሲያ በዩክሬን ላይ ባካሄደችው ከፍተኛ የ ሚሳኤል እና የድሮን ጥቃት ሕፃናትን ጨምሮ ቢያንስ ስምንት ሰዎች ተገደሉ።

  • Wednesday · 11 min

    የሐምሌ 22 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    -ሳዑዲ አረቢያ «ሐሺሽ ይዘዉ ተገኝተዋል» በሚል የወነጀለቻቸዉን አምስት ኢትዮጵያዉያን ሥደተኞችን በሞት ቀጣች።ሑዩማን ራይትስ ዋች እንዳስታወቀዉ ሳዑዲ አረቢያ የግሪጎሪያኑ 2026 ከባተ ካለፈዉ ጥር ወዲሕ በተመሳሳይ ወንጀል ተሳትፈዋል ያለቻቸዉን 17 ኢትዮጵያዉያንን ያለ ተገቢ የፍርድ ሒደት በሞት ቀጥታለች።----የተለያዩ የወንጀል መረቦች «ሥራ ታገኛላችሁ» በሚል ከየሐገሩ እያስኮበለሉ በየማጭበርበሪያ ማዕከላቱ የሚሰቃዩና የሚያሰሯቸዉ ሰዎች ብዛት በመቶ ሺሕ ሊቆጠር እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።---ዩናይትድ ስቴትስ ከኢራን ጋር በገጠመችዉ ጦርነት ሳዑዲ አረቢያም ቀስ በቀስ እየተዘፈቀችበት ነዉ።

  • July 28 · 12 min

    የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ

    አርስተ ዜና፤ አዲስ አበባ ላይ ለሁለት ቀናት የሚዘልቀው 49ኛው የአፍሪቃ ኀብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባዔ፣ አህጉሪቱን ለገጠሟት የፀጥታ ችግሮች ትኩረት መስጠት እንዳለበት ተነገረ። -መቀመጫቸዉን ቤንጋዚ የያደረጉ የሊቢያ ባለሥልጣናት፣ የተለያዩ ዜግነት ያላቸውን ቢያንስ 117,350 ሕገ-ወጥ ያሏቸውን ስደተኞች ከአገር ማባረራቸዉን ገለፁ። በሌላ በኩል ከ100,000 የሚበልጡ ፈቃደኛ ሱዳናውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ ተመዝግበዋል።-ጠ/ሚቤንያሚን ኔታንያሁና የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በሟቹ የአሜሪካ የምክር ቤት አባል የሐዘን ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ዋሽንግተን ገቡ።

  • July 27 · 10 min

    የሐምሌ 20 ቀን፤ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    የዛሬው የዓለም ዜና ፤በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ አርሲ ከ450 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመጉ ይፋ ማድረጉን፣የናይጄሪያ ጦር በታጣቂ ቡድን የተጠለፉ 48 ሰላማዊ ሰዎችን በዘመቻ ማስለቀቁን፣በኢራን የሚደገፉት የየመን የሁቲ አማፂያን በሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ መሠረተ ልማት ላይ የድሮን ጥቃቶች መጀመራቸውን፣የጀርመን መራሄ መንግስት ፍሬድሪሽ ሜርዝ ቅዳሜ በበርሊን በተፈፀመው ጥቃት ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪ ማቅረባቸውን ፣ኢራን ከአሜሪካ ጋር ምንም አይነት ድርድር ውስጥ እንዳልሆነች መግለጿን እንዲሁም በአሜሪካ ሲያትል በተካሄደ የምግብ ፌስቲቫል በተኩስ ልውውጥ ቢያንስ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን አካቷል።

  • July 26 · 8 min

    የሐምሌ 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    የዛሬው የዓለም ዜና ፤ከባድ የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትለው «ሱፐር ኤል ኒኖ» በአፍሪካ ሃገራት ላይ ከ10 እስከ 20 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን የኢኮኖሚ ጉዳት ያደርሳል መባሉን፣በበርሊን የተፈፀመው ጥቃት ከሽብር ጋር የሚይያያዝ ነው ሲል የጀርመን ፖሊስ መግለፁን፣በፈረንሳይ ሰደድ እሳት 250,000 በላይ ሰዎችን ማፈናቀሉን እንዲሁም ብራዚል ከምርጫ በፊት የአሜሪካ ባለስልጣናት ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ መከልከሏን አካቷል።

  • July 25 · 10 min

    የሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

    • በኮንጎ በኤቦላ ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ3000 ማለፉ በተሰማበት በዛሬው ዕለት (ቅዳሜ) የጤና ባለሞያዎች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ ። • የየመኑ ሁቲ አማፅያን በሳዑዲ አረቢያ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ተቋማት ላይ የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃት መፈጸማቸውን አስታወቁ። • ሩስያ እና ዩክሬን አንዳቸው በሌላው ላይ በደረሷቸው የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃቶች ከበርካታ ሰዎች ተገደሉ። • በደቡባዊ ምዕራብ ፈረንሳይ የተቀሰቀሰው የሰደድ እሳት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ ባለስልጣናት ነዋሪዎችን ከአካባቢው ማስለቀቅ ጀመሩ።

  • July 24 · 12 min

    የዕለተ ዐርብ ሐምሌ 17 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    የአፍሪቃ ኅብረት በቀይ ባሕር የተፈፀመውን የመርከቦች ጥቃት አወገዘ፤ ጋሮዌ፥ የአደን ባሕረ ሠላጤ የየመን ክልል ላይ የታገተችው የንግድ መርከብ በሶማሌ የባሕር ላይ ወሮበሎች ቁጥጥር ስር ናት፤ ኪንሻሳ፥ የዘንድሮው የኢቦላ ወረርሺኝ ከከዚህ ቀደሙ በሦስት እጥፍ የተፋጠነ ነው፤ ቤርሊን፥ የጀርመን መንግሥት የካቢኔ አባላት ለውጥ አደረ፤ ማድሪድ፦ በዐሥር ሺህዎች የሰደድ እሳት ፍራቻ ተፈናቅለዋል፤ ቤርሊን፥ ዬርገን ክሎፕ የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ኾኑ

  • July 23 · 11 min

    የሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    የሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ በሚገኘው አባይ ገዳመ አስቄጤስ አቡነ አረጋዊ እና ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም ላይ ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ተፈፀመ በተባለ የድሮን ጥቃት የ2 መነኮሳት ህይወት ማለፉን የገዳሙ አበምኔትና የወረዳዉ ቤተክህነት ኃላፊ ተናገሩ። በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማጽያን ዛሬ ቀይ ባህር ላይ በነበሩ ሁለት የሳዑዲ አረብያ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተናግረዋል። ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን ትናንት የተፈራረሙት ስምምነት ሳዑዲ አረብያ ከእስራኤል ጋር መደበኛ ግንኙነት እንዲኖራት የሚጠይቅ መሆኑን ትራምፕ አስታወቁ።

  • July 22 · 11 min

    የሐምሌ 15 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    -የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ «አደገኛ የሰዉ አዘዋዋሪ ወንጀለኛ» ያለዉን 17 አባላት ያሉት መረብን መበጣጠሱን አስታወቀ።---የዓለም የረሐብተኞች ቁጥር አምና ለሶስተኛ ተከታታይ ዓመት መቀነሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።የረሐብተኛዉ ቁጥር ቢቀንስም የዓየር ንብረት መዛባትና የንግድ መደናቀፍ የረሐብተኛዉን ቁጥር እንደገና ሊያንረዉ ይችላል።-ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን የገጠሙት ጦርነት የባብ ኤል መንደብን መስመርም አዘግቷል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ተፋላሚዎች የሲቢል ተቋማትን እንዳይመቱ ተማፅነዋል።የአሜሪካ ፕሬዝደንት ግን የኢራንን ድልድዮችና የነዳጅ ተቋማት ለማዉደም እየዛቱ ነዉ።

  • July 21 · 10 min

    የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ

    አርስተ ዜና፤ ኢሕአፓ በትግራይ አዲስ የጦርነት ሥጋት ማንዣበቡን በመግለፅ ጥሪ አቀረበ። ፓርቲው መንግሥት በሚያስተዳድራቸው መገናኛ ብዙኃን የሚካሄድ ያለው "የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እና የሕዝብን ሥነ-ልቦና ለጦርነት የማዘጋጀት ሙከራ" ከአራት ዓመታት በፊት በትግራይ ጦርነት ዋዜማ ከታየው ሂደት ጋር አንድ አይነት ነው"ብሏል።- የአራት ቀናት አፍሪቃ ሃገራት ጉብኝታቸዉን ከሞሪታንያ የጀመሩት የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮሃን ቫዴፉል የሞሪታንያ ጉብኝታቸዉን አጠናቀዉ ናይጀርያ ገብተዋል። ሚኒስትሩ አገራቸዉ እና ሞሪታኒያ በንግድ፣ በኃይል ቀርቦትና በደኅንነት ዘርፎች ላይ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠነክሩ ገልፀዋል።

  • July 20 · 11 min

    የሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    የሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና ከሱዳኑ ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ጋር በምታካሂደው ጦርነት ኬሚካዊ የጦር መሣሪያዎችን ጥቅም ላይ አውላለች ባለቻት በሱዳን ላይ ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ አዲስ ማዕቀብ ጣለች።ለክሱ ያቀረበችው ማስረጃ ግን የለም ተብሏል። ዛሬ የተመረጡት አዲሱ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርንሀም መንግሥት እንዲመሰርቱ በንጉሥ ቻርልስ ሣልሳዊ ተጠየቁ። የቀድሞ የግሬተር ማንቼስተር ከንቲባ የ56 ዓመቱ በርንሀም ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት የሌበር ፓርቲ መሪነት ከተመረጡ ከ3 ቀናት በኋላ ነው። የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ አሸናፊ የስፔን ቡድን ዛሬ ወደ ሀገሩ ሲመለስ የጀግና አቀባበል ተደርገለት።

  • July 19 · 7 min

    DW Amharic የሐምሌ 12 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    በሶማሌ ክልል ቀብሪ በያሕ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ። ለ2019 የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት 704 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ። በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ምዕራባዊ ክፍሎች፤ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልና በጋምቤላ ክልል በተወሰኑ አካባቢዎች በሚጥል ከባድ ዝናብ ምክንያት የጎርፍ መጥለቅለቅ ሊከሰት እንደሚችል የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስጠነቀቀ። የታንዛኒያ ሰንደቅ የሚያውለበልብ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ከየመን የባሕር ዳርቻ በሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎች ታገተ። አሜሪካ ሁለት ወታደሮቿ በዮርዳኖስ ከተገደሉ በኋላ ኢራንን “ለመቅጣት” አዲስ ዙር የለሊት የአየር ላይ ድብደባ ፈጸመች።

  • July 18 · 10 min

    የሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ-ም የዓለም ዜና

    የዛሬው የዓለም ዜና ፤በአዲስ አበባ ከተማ ህወሓትን የሚቃወም ሰልፍ መካሄዱን፤ኢራን 'የአሜሪካ ጥቃቶች ከቀጠሉ ምንም አይነት የፖለቲካ ድንበር ደህንነቱ የተጠበቀ አይሆንም' ስትል ማስጠንቀቋን፣የሊባኖስ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ለማግኘት ወደ ዋሽንግተን ማቅናታቸውን፤በጀርመን ከፍተኛ የሽብር ስጋት መኖሩን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር መግለፁን፣ዩክሬይን በሁለት የሩስያ ግዛቶች ሌሊቱን ለዛሬ አጥቢያ ፈጸመችው በተባለ የድሮን ጥቃቶች 9 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የሩስያ ባለስላጣናት ማስታወቃቸውን እንዲሁም ህንድ የመጀመሪያውን የግል ሮኬት ወደ ህዋ ማምጠቋን አካቷል።

  • July 17 · 11 min

    የሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    በዛሬው የዓለም ዜና፤ የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂና የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ-መንበር አብደል ፋታኅ አል ቡርኻን በአስመራ መገናኘታቸውን፣ሶማሊያ በየኮቪድ-19 ሰበብ የ250 ሚሊዮን ዶላር ማጭበርበር የተከሰሰ ቁልፍ ተጠርጣሪን ለአሜሪካ አሳልፋ መስጠቷን፣የኢራን አብዮታዊ ዘብ በዮርዳኖስ የአሜሪካን አውሮፕላኖችን በሚሳኤልና በድሮን መምታቱን፣ አንዲ ቡርንኻም በብሪታኒያ በሥልጣን ላይ የሚገኘው ሊበር ፓርቲ መሪ ሆነው መመረጣቸውን እና ቻይና አሜሪካ በጋዜጠኞች የቆይታ ጊዜ ላይ በጣለችው ገደብ ላይ 'የአፀፋ እርምጃዎችን' እንደምትወስድ ማስጠንቀቋን አካቷል።

  • July 16 · 9 min

    የሐሙስ ሐምሌ 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    አ.አ፥ ስለተጀመረው አገራዊ ምክክር የፓርቲዎች ትችት እና ድጋፍ፤ ሙዋንጋ ፥ ዛምቤዚ ባህር ሰጥመዋል የተባሉ ኢትዮጵያዉያን በሕይወት ተገኙ፤ ዋሽንግቶን፥ ዩናይትድ ስቴትስ በኢቦላ ከተጠቃችው ኮንጎ የሚመጡ ዜጎቿን ወደ አገር መግባት ከለከለች፤ ኪዬቭ፥ አዲስ ጠቅላይ ሚንሥትት ተሾሙ፥ መከላከያ ሚንሥትሩ ተሻሩ፤ቴሕራን፥ ኢራን ዩናይትድ ስቴትስ ስትደበድባት የባህረ ሠላጤው አገራት ላይ ጥቃቷን አጠናከረች፤ ሣንዓ፥ የሑቲ ዓማጺያን የሣዑዲ ዓረቢያን እንደሚደበድቡ ዛቱ