Artwork for የዓለም ዜና
News

የዓለም ዜና

DW

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።

  • 100 episodes
  • Updated Yesterday

Episodes100

  • June 25 · 12 min

    የሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    የኬንያ ፖሊስ በዛሬው ዕለት ናይሮቢ በሚገኘው ዋና የፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ የተሰበሰቡ ሰልፈኞችን በአስለቃሽ ጭስ በተነ። ቬንዝዌላን ባናወጠው የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ የ164 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን 971 ሰዎች መጎዳታቸውን የሀገሪቱ ጊዜያዊ ፕሬዝደንት አስታወቁ። በርካታ ሃገራት ለእርዳታ እጃቸውን ዘርግተዋል። የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ እስራኤል ከመላ ሊባኖስ መውጣት እንደሚኖርባት አመለከቱ። እስራኤል ሂዝቦላህ ትጥቁን ሳይፈታ ኃይሌን አላወጣም ብላለች። ፈረንሳይ ከሩሲያ ጋር ግንኙነት ያለው ነዳጅ ጫኝ መርከብን በሲሲሊ የባሕር ዳርቻ ላይ መያዟን አስታወቀች። ሩሲያ ድርጊቱን አውግዛ የባሕር ላይ ውንብድና ብላዋለች።

  • June 24 · 11 min

    የሰኔ 17 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    -ራሱን የሊቢያ «የመረጋጋት መንግሥት» ብሎ የሚጠራዉ የምሥራቅ ሊቢያ ስብስብ የኢትዮጵያ፣ የሶማሊያ፣ የኤርትራና የሱዳን ዜጎች ሊቢያ እንዳይገቡ አገደ።---አዉሮጳን የገለበዉ የሙቀት ማዕበል የሰዎች ሕይወት እያጠፋ፣የትምሕርት ሒደት፣ሥራና እንቅስቃሴንም እያስተጓጎለ ነዉ።አለቅጥ የናረዉ ሙቀት ያንገበገባቸዉ አንዳድ ሰዎች ዘለዉ ወንዝ፣ኩሬና ገንዳ ዉስጥ እየገቡ ሞተዋል።--የዓለም የአዉቶሚክ ተቆጣጣሪ ድርጅት (IAEA) የኢራንን የኑክሌር ተቋማትና ንጥረ ነገር በቅርቡ እንደሚፈትሽ አስታወቀ።ኢራን ግን የኑክሌር ጉዳይ የሚነሳዉ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያደረገችዉ ሥምምነት ገቢራዊነት ሲረጋገጥ ብቻ ነዉ ትላለች።

  • June 23 · 9 min

    የሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ ም የዓለም ዜና

    ግብፅ ከህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ጋር በተያያዘ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር አዋለች።ዩጋንዳ ውስጥ አንድ አዲስ ሰው ላይ ኤቦላ ተረጋገጠ፤ በጠቅላላው 20 ሰዎች ተይዘዋል እስራኤል ወደፊት የጦር መሣሪያ አቅርቦትን በተመለከተ የዩናይትድ ስቴትስ ጥገኛ መሆን እንደማትፈልግ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ አስታወቁ። አምስት ልዑካንን ያቀፈ የታሊባን ቡድን ዛሬ ከአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ተወካዮች ጋር ለመምከር ብራስልስ ገባ። ዶይቸ ቬለ DW በየዓመቱ የሚያካሂደው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ ዛሬ ማክሰኞ በቦን ከተማ መካሄድ ጀመረ።

  • June 22 · 9 min

    የሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

    የኬንያ የሰራተኛ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ወጣቶችን ለሩስያ በወታደርነት በመመልመል እንደሚጠረጠሩ ተገለጸ። በቀጠር በአንድ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ በደረሰ ፍንዳታ 13 ሰዎች ሲሞቱ በ 54 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የቀጠር የሐገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። በዮናይትድ ስቴትስና ኢራን መካከል በስዊዘርላንድ ሲካሄድ የነበረ ንግግር በጥሩ መንፈስ መጠናቀቁን የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቁ።የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣናቸውንና ከሌበር ፓርቲ መሪነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው እንደሚለቁ አስታወቁ።

  • June 21 · 6 min

    የሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    የዛሬው የዓለም ዜና በአብዛኛዎቹ አካባቢዎች ገዡ ፓርቲ ብልፅግና 90 በመቶ ድምፅ ማግኘቱን ምርጫ ቦርድ መግለጹን፣በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነፃ እና ገለልተኛ ተቋም ሆኖ መስራቱን የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ መናገራቸውን፣በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሴቶች ያለስጋት እንዲሳተፉ ሁሉን አቀፍ ርምጃ ተወስዷል ሲል የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ማለቱን እና በምርጫ ወቅት ጥቃቶች መፈፀማቸውን መጠቆሙን እንዲሁም ገዥው ፓርቲ ብልፅግና በቀጣይ አምስት የስልጣን አመታት የነበሩ ችግሮችን እንዲቀርፍ ነዋሪዎች መጠየቃቸውን አካቷል። # ምርጫ2018 #EthiopiaElection2026

  • June 20 · 10 min

    የሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

    • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤርትራ ጉዳይ ልዩ መርማሪ በሀገሪቱ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተባባሰ መምጣቱን አስታወቁ። • በእስር ላይ የነበረችው ጋዜጠኛ ሳልሳዊት ባይነሳኝ መፈታቷን ቤተሰቦቿ ለዶቼ ተናገሩ። • በምስራቃዊ ሊቢያ የባህር ዳርቻ የአንድ ህጻን ሴት ልጅን ጨምሮ በትንሹ የ15 ፍልሰተኞች አስከሬን ተገኘ። • አፍሪካ እና የካሪቢያን ሀገራት መሪዎች ጥቁሮችን ለባርነት የዳረጉ ያሏቸውን ሃገራት ካሳ እንዲከፍሉ ጠየቁ ። • ኢራን የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥን በድጋሚ ዘጋች። • አውሮጳን እያናወጠ የሚገኘው አስከፊ የሙቀት ማዕበል በጀርመን ፣ፈረንሳይ እና ጣልያን ብርቱ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተነገረ።

  • June 19 · 11 min

    የሰኔ 12፣ ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

    • በትግራይ ክልል ለወታደራዊ ስልጠና የሚደረገው የአፈሳ ዘመቻ ብርቱ ትችት እና ተቃዉሞ መቀስቀሱ ተዘገበ ። • በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ዛሬ ዓርብ አስጠነቀቀ። • እስራኤል እና የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ ቀደም ሲል አድርገው የነበረውን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማደስ መስማማታቸው ተገለጸ። • የአውሮጳ ኅብረት መሪዎች በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ዙሪያ የኅብረቱን ጥቅሞች ለማስከበር ከሩስያ ጋር ቀጥተኛ ያልሆነ ግንኙነት ለመጀመር ያቀረቡት ሐሳብ ሳይሳካ ቀረ።

  • June 18 · 10 min

    የሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    አርዕስተ ዜና -ዩናይትድ ስቴትስ «አክራሪ» ባለቻቸዉ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባላትና በቤተሰቦቻቸዉ ላይ ያነጣጠረ የቪዛ እገዳ ጣለች። ዩናይትድ ስቴትስ የቪዛ እገዳዉን የጣለችዉ / በትግራይ ክልል ሠላም ለማስፈን የተደረገዉን ስምምነት በሚጥሱና ከሚጥሱ ወገኖች ጋር በሚተባበሩ ሰዎች ላይመሆኑን አስታውቃለች። -የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፈዉ ግንቦት በተደረገዉ ምርጫ ሒደት ቅሬታ ከቀረበባቸዉ 128 የምርጫ ክልሎች ለ85ቱ ዉሳኔ መስጠቱን ዐሳወቀ። -በኤልኒኞ ምክንያት ኢትዮጵያውያን ጨምሮ 22 ሀገራት ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸውን FAO እና የWFP ዛሬ በጋራ አሰሳቡ።

  • June 17 · 10 min

    የሰኔ 10 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    -የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያስገነባችዉ ግድብ ግብፅን ለብዙ ችግሮች አጋልጧል አሉ።ትራምፕ የግብፅ አቻቸዉን ዛሬ ሲያነጋግሩ እንዳሉት መስተዳድራቸዉ ሁለቱን ሐገራት ለማግባባት እንደሚጥር አስታዉቀዋልም።---በ13 ሐገራት ወይም ግዛቶች የሚኖር በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ አስቸኳይ ርዳታ ካላገኘ ለአስከፊ ረሐብ እንደሚጋለጥ የተባበሩት መንግሥታት ሁለት ድርጅቶች አስታወቁ።ድርጅቶቹ እንደሚሉት ሱዳን፣ ሶማሊያና ጋዛን ጨምሮ ለችግር የተጋለጡ 266 ሚሊዮን ሰዎች በቂ ርዳታ አያገኙም።---የቡድን 7 አባል ሐገራት መሪዎች በማደግ ላይ ባሉ ሐገራት ላይ ያለዉን ዕዳ ለማቃለል ቃል ገቡ።

  • June 16 · 12 min

    የሰኔ 9 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    በዚምባብዌ አንድ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከባቡር ጋር በመላተሙ ቢያንስ 9 ሰዎች ሲሞቱ 25 መቁሰላቸውን የሐገሪቱ የሐገሪቱ ባለስልጣናት አሳወቁ። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሐገራቸው ከአሜሪካ ጋር የመጨረሻው የሰላም ስምምነት በመጨው አርብ በስዊትዘርላንድ እንደሚፈረም አረጋገጡ።ዩክሬን በሞስኮ አቅራቢያ የሚገኘውን የሩስያ የነዳጅ ማጣሪያ ማጋየቷ ተሰማ። ጀርመን ወደ 30 የሚሆኑ የአፍጋኒስታን ዜጎች ከሐገር ማባረሯን አሳወቀች።

  • June 15 · 12 min

    DW Amharic የሰኔ 08 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    ከደሴ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የሕዝብ ማጓጓዣ አውቶቡስ 170 ሜትር ርዝመት ያለው ገደል ውስጥ በመውደቁ የ31 ሰዎች ሲሞቱ 30 ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደረሰባቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቢሾፍቱ አቅራቢያ እየተገነባ በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ምክንያት “የሚጎዳ አርሶ አደር” እንደማይኖር ቃል ገቡ። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ፎልከር ቱርክ በሱዳን ጦርነት የድሮን አጠቃቀም ላይ የታየውን “ከፍተኛ ጭማሪ” አወገዙ። ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን የገጠሙትን ጦርነት ለማብቃት ከሥምምነት መድረሳቸውን አሳወቁ። ሩሲያ በዩክሬን ከተሞች ላይ በሚሳይሎች በፈጸመችው ጥቃት11 ሰዎች ተገደሉ።

  • June 14 · 7 min

    የሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

    የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት አብዲራሕማን ሞሐመድ አብዱላሒ "ታሪካዊ" የተባለለትን ጉብኝት እውቅና በሰጠቻቸው ሀገር እስራኤል እያደረጉ ነው። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብቻ ከ 700 በላይ ሰዎች በኢቦላ ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ። የእስራኤል ጦር ዛሬ የሂዝቦላህ ቡድንን ለማጥቃት የሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ደቡባዊ ክፍልን ከአየር ደበደበ። ቡድኑ አስቀድሞ ዛሬ ጠዋት በሰሜናዊ እስራኤል የድሮን ጥቃት ፈፅሟል። የኢራን ዋና ተደራዳሪ ሞሐመድ ባግኸር ጋሊባፍ በዚህ አይነት ሁኔታ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የሰላም ድርድሩን መቀጠል ፋይዳ እንደማይኖረው ተናገሩ።

  • June 13 · 10 min

    የሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

    • የኤርትራው የማስታወቂያ ሚንስትር የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ብልጽግና ፓርቲ በተዛባ መረጃ ላይ የተመሰረተ ፕሮፖጋንዳ ያሰራጫል ሲሉ ከሰሱ ። • በኢራን እየተካሄደ ያለው ጦርነት የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋን በመናርና የአቅርቦት እጥረትን በመፍጠር በአፍሪካ አየር መንገዶች ላይ ከፍተኛ ቀውስ እየደቀነ መሆኑን የአፍሪካ አየር መንገዶች ማኅበር (AFRAA) አስጠነቀቀ። • ዩጋንዳ በኤቦላ ወረርሽኝ ምክንያት በአሜሪካ እና በሌሎች ሀገራት የተጣለባትን የአየር ጉዞ እገዳ «ኢ-ፍትሐዊ» ስትል ኮነነች። • የኒጀር ወታደራዊ ሁንታ ግብረ-ሰዶማዊነትን በወንጀል የሚቀጣ አዲስ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ማውጣቱን አስታወቀ።

  • June 12 · 11 min

    የሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    በአፍሪቃ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የተመራ የልዑካን ቡድን ወደ መቀለ መጓዙ ተሰማ። የቡድኑ መሪ የጉዟቸው ዓላማ ሁኔታዎች እንዳይባባሱ አስቀድሞ ለማርገብ ነው ብለዋል። የትግራይ ክልል ባለሥልጣናት ለዳግም ጦርነት እየተዘጋጁ ነው መባሉን ውድቅ ማድረጋቸው ተዘገበ። «ላ ክሯ» ለተሰኘ ጋዜጣ የምትዘግብ ፈረንሳዊት ጋዜጠኛ ከኢትዮጵያ መባረሯን ድርጅቱ አመለከተ። የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን አሾልካ አወጣች ያሉት የስምምነት በጽሑፍ ያለውን ውል የሚወክል አይደለም አሉ። የኢራን ባለሥልጣናት በበኩላቸው ጣላቶቻችን ያሏቸው አሜሪካን እና እስራኤል ከኃይል በቀር የድርድር ቋንቋ አይገባቸውም ብለዋል።

  • June 11 · 11 min

    የሐሙስ ሰኔ 4 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    መቐለ፥ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ኦሉሴጉን ኦባሳንጆን ዛሬ መቐለ ከተማ ዉስጥ ተቀብለው አነጋገሩ፤ አ.አ፥ ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት ከ2.3 ትሪሊዮን ብር በላይ ለፕላን-በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመራ፤ ጂዳ፥ ሣዑዲ ዓረቢያ ታስረው የነበሩ 1,655 ኢትዮጵያውያን ምሕረት አገኙ፤ የአሜሪካ ጦር በሁለተኛው ቀን ኢራን ውስጥ በርካታ ኢላማዎችን እየመታ መሆኑን ዐሳወቀ፤ ኬፕታውን፥ የኬፕ ታውን ማራቶን ከዓለማችን ታላላቅ የማራቶን ውድድሮች መካከል አንዱ ኾነ፤ ሜክሲኮ ሲቲ፥ የዓለም እግር ኳስ ጨዋታ በደቡብ አፍሪቃ እና በሜክሲኮ መካከል ዛሬ ማታ ይከፈታል

  • June 10 · 10 min

    የሰኔ 3 ቀን፣ 2018 የዓለም ዜና

    -ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክና ዩጋንዳ ዉስጥ የተሰራጨዉ የኢቦላ ተሕዋሲ የያዛቸዉ ሰዎች ቁጥር 620 ደረሰ።ተሕዋሲዉ 120 ያክል ሰዎች መግደሉ ተረጋግጧል።ሶስት የኮንጎ ቤተ-ምርመራዎች ተሕዋሲዉን መመርመሪያ መሳሪያና ንጥረ-ነገር አልቆባቸዋል።---ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን እንዳዲስ መደባደብና መዛዛት ይዘዋል።የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የኢራን ወታደራዊ ተቋማት ያላቸዉን ሥፍራዎች ሲደበድብ፣ ኢራን ባፀፋዉ ከባሕሬን እስከ ዮርዳኖስ የሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሠፈሮችን ደብድባለች።----ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገባ የተከለከለዉ ሶማሊያዊ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ግጥሚያ ዳኛ ሞቃዲሾ ሲመለስ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።

  • June 9 · 12 min

    የዓለም ዜና፤ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ

    አርስተ ዜና--በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የተፈናቃዮች ልዩ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በአማራ ክልል ዛሬ ተከናወነ። ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በነበሩ የፀጥታ ችግር ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸዉ እንዲመለሱ ጠይቀዋል።-በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል ተባብሶ እንደቀጠለ የተገለፀውን ውጥረት በተመለከተ፣ የፕሪቶሪያውን ግጭት በዘላቂነት የማቆም የሰላሞ ስምምነት በዋነኛነት ከመራው የአፍሪቃ ኅብረት በኩል እስካሁን የወጣ መግለጫም ይሁን የተሰጠ አስተያያት የለም።-የዓለም ዋንጫ ጨዋታን ለመምራት ለሀገሩ የመጀመሪያው ለመሆን የተዘጋጀው ሶማሊያዊ ዳኛ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ተከለከለ።

  • June 8 · 10 min

    የሰኞ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ደቡብ አፍሪቃ በሚገኙ ስደተኞች ላይ ከሕግ በላይ ሆነው እርምጃ የሚወስዱትንሰዎች ባለሥልጣናቶቻቸውእንደማይታገሱ አሳሰቡ ። ኢራን እስራኤልን ትናንትናና ዛሬ ስትደበድ እሥራኤልም በአጸፋው ኢራንን ዛሬ መታለች ። ትናንት ወደ እሥራኤል ሮኬቶችን በተመተኮስ ማጥቃት የጀመረችው ኢራን 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የመከላከል ዘመቻውን እንደምታቆም አስታውቃለች። ከእሁዱ የኢራን ጥቃት በኋላ የእሥራኤል ጦር ዛሬ (መጠነ ሰፊ) ያለውን ጥቃት በኢራን ላይ መፈጸሙን ገልጿል። ማልታ አቅራቢያ በሰጠመች ጀልባ ውስጥ የነበሩ ቢያንስ 11 ስደተኞች ሞቱ። ወደ 50 የሚሆኑ ደግሞ ተረፉ።

  • June 7 · 9 min

    የግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    የማዕከላይ አፍሪካ ሪፐብሊክ መንግስት ከአሜሪካ የሚጠረዙ ስደተኞችን ተቀብሎ ለማስተናገድ መስማማቱን ከሐገሪቱ የወጡ ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች አረጋገጡ። ዩናይትድስቴትስና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት ዛሬ 100 ቀናትን ደፍኗል። ዩናይትድ ስቴትስ በተለያዩ ባንኮች ታግዶ የሚገኘውን የኢራን ሐብት፤ በኢራን የሚሳይልና የድሮን ጥቃት ለደረሰባቸው የባህረ ሰላጤ ሀገራት እንዲውል ማቀዷን አስታወቀች።

  • June 6 · 8 min

    DW Amharic-የቅዳሜ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    የዛሬው የዓለም ዜና ፣የኢትዮጵያ አየር ሃይል በትግራይ ክልል ሸራሮ ከተማ አቅራቢያ አካሄደው በተባለው የድሮን ጥቃት ጉዳት ደረሰ መባሉን።ናይጄሪያ እና ጋና ዜጎቻቸው ደቡብ አፍሪካን ለቀው እንዲወጡ ሀሳብ ማቅረባቸውን፣ኩዌት፤ አዲሱ የኢራን ጥቃት 'አደጋ የሚያባብስ ' መሆኑን መግለጿን።በጀርመን በፖለቲካዊ መነሻ የሚፈጸም ወንጀል በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል መባሉን፣የሮማው ሊቃነ ጳጳስ በዓለም ላይ ዋልታረገጥነ አስተሳሰብ እንዲያበቃ ጥሪ ማቅረባቸውን እንዲሁም ኢራን ቅዳሜ ዕለት ቱርክን ለቀው ወደ ሜክሲኮ ከሚያመሩት ተጫዋቾቿ ጋር ለሚጓዙት የዓለም ዋንጫ ቡድን የድጋፍ ሰራተኞች ቪዛ በመከልከሏ አሜሪካን ክፉኛ መቸቷን አካቷe።