የዓለም ዜና

የሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

June 25 · 12 min · 13.6 MB
0:00-12:33

Streams straight from the publisher. podnod never proxies or re-hosts episode audio.

የኬንያ ፖሊስ በዛሬው ዕለት ናይሮቢ በሚገኘው ዋና የፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ የተሰበሰቡ ሰልፈኞችን በአስለቃሽ ጭስ በተነ።
ቬንዝዌላን ባናወጠው የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ የ164 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን 971 ሰዎች መጎዳታቸውን የሀገሪቱ ጊዜያዊ ፕሬዝደንት አስታወቁ። በርካታ ሃገራት ለእርዳታ እጃቸውን ዘርግተዋል።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ እስራኤል ከመላ ሊባኖስ መውጣት እንደሚኖርባት አመለከቱ። እስራኤል ሂዝቦላህ ትጥቁን ሳይፈታ ኃይሌን አላወጣም ብላለች።

ፈረንሳይ ከሩሲያ ጋር ግንኙነት ያለው ነዳጅ ጫኝ መርከብን በሲሲሊ የባሕር ዳርቻ ላይ መያዟን አስታወቀች። ሩሲያ ድርጊቱን አውግዛ የባሕር ላይ ውንብድና ብላዋለች።