Artwork for የዓለም ዜና
News

የዓለም ዜና

DW

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።

  • 100 episodes
  • Updated Monday

Episodes100

  • July 15 · 10 min

    የሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ተጀምሯል። ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ « ለእኔ ሳይሆን ለእኛ፣ ለኢትዮጵያ ማለት ከቻልን ምክክሩ ፍሬያማ ይሆናል በማለት ለጉባኤተኞቹ ጥሪ አቅርበዋል። ወደቦትስዋና ለመሻገር የሞከሩ 10 ኢትዮጵያውያን የተሳፈሩባት ታንኳ ተገልብጣ ሳይሰጥሙ እንዳልቀረ የዛምብያ ባለሥልጣናት ዛሬ አስታወቁ። በታንኳዋ ተሳፍረው ከነበሩት 15 ኢትዮጵያውያን አስሩ ሰጥመዋል ተብሎ እንደሚታመን የተናገረው ፖሊስ ሦስት ደግሞ የደረሱበት እንዳልታወቀ ገልጿል። ከመካከላቸው በህይወት የተረፉትን ሁለቱን ፖሊስ አስሯቸዋል። የዩናይትድ ስቴትስ እና የኢራን ጥቃትና የአጸፋ ጥቃት ዛሬም ቀጥሏል።

  • July 14 · 12 min

    የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 7 ቀን 2028 ዓ.ም ማክሰኞ

    አርስተ ዜና-የአሜሪካ ጦር ለሦስተኛ ተከታታይ ምሽት በኢራን ኢላማዎች ላይ ጥቃቶችን ማካሄዱን አስታወቀ። የኢራን አብዮታዊ ዘብ በበኩሉ ፤ በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ሁለት ከፍተኛ ነዳጅ መርከቦችን መምታቱን እና ከጉዞ ማሰናከሉን አስታውቋል።-ከስድስት ዓመት በላይ ከኦሮሚያ ክልልና ሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞን በመጠለያ ጣቢያና ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ ከ60 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ለከፍተኛ የምግብ ዋስትና ሥጋት መጋለጣቸውን ተናገሩ።-አውሮጳ ህብረት በሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ላይ የሚዉለዉን የገንዘብ ድጋፍ ለመቀነስ በሱዳን የወርቅ ንግድ ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለ።

  • July 13 · 12 min

    የሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

    የኢትዮጵያ የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል እየተፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በአስቸኳይ በማስቆም ሕገ መንግስታዊ ግዴታውን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አሳሰበ። የየመን ሑቲ ታጣቂዎች ሳውዲ ዓረብያ በሰነዓ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ«ፈጸመችው» ላሉት ጥቃት አጸፋዊ ምላሽ እንደሚሰጡ አስጠነቀቁ። አሜሪካ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በሆርሙዝ ሰርጥ «እየፈጸመው ነው» ላለችው ማስተጓጎል ያስታገሰ ያለችውን ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች። ኢራን በበኩሏ በዮርዳኖስ፣ ባሕረይና ኩዌት የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮችን ደብድባለች።

  • July 12 · 8 min

    የሐምሌ 5 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

    • የሱዳን ፍርድ ቤት መሐመድ ሐምዳን ዳግሎን ጨምሮ 16 የፈጥኖ ደራሹ ኃይል RSF አመራር በሌሉበት የሞት ቅጣት ፈረደ። • ደቡብ አፍሪካ ሶስት የቤተሰቡን አባላት በመግደል ሸሽቶ ወደ ሐገሯ ገብቶ የነበረውን ብሪታንያዊ አሳልፋ ልትሰጥ ነው። • የኢራን አብዮታዊ ዘብ የሆርሙዝ ሰርጥ መዝጋቱን አስታወቀ። • የእስራኤል ጦር ኃይል በጋዛ ሰርጥ ባደረሳቸው ጥቃቶች አንዲት የ9 ዓመት ሴት ልጅን ጨምሮ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጤም የጤና ባለስልጣናት አስታወቁ። • የቀድሞው የቃጣር መሪ ሼክ ሐማድ ቢን ኻሊፋ አል ታኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ። 74 ዓመታቸው ነበር ።

  • July 11 · 10 min

    DW Amharic የሐምሌ 04 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    አሜሪካ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለስድስት አገራት ዜጎች የተሰጠውን በአገሪቱ የመቆየትና የመሥራት ጊዜያዊ ከለላ ለተጨማሪ ቀናት አራዘመች። የሱዳን ብሔራዊ ጦር አሜሪካ ያዘጋጀችውን ምክረ-ሐሳብ የሚቀበለው ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከተቆጣጠራቸው ከተሞች ለቅቆ ሲወጣ እንደሆነ ቅድመ-ሁኔታ አስቀመጠ። የናይጄሪያ ጦር በዛምፋራ ከ300 በላይ ታጣቂዎች ገደለ ተባለ። የኢራን መንፈሳዊ መሪ ሞሽታባ ኻሜኒ አገራቸው የአባታቸውን ገዳዮች መበቀሏ “አይቀሬ” እንደሆነ ዛቱ። የአሜሪካው ፕሬዝደንት በኢራን ላይ ያነጣጠሩ 1,000 ሚሳይሎች መጠመዳቸውን አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች ስድስት ሰዎች ሲገደሉ 29 ቆሰሉ።

  • July 10 · 10 min

    የሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    የሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና ከዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኢኩዋቶርያል ጊኒ የተጠረዙ ከኢትጵዮያ፣ከአንጎላ እና ከሞሪቴንያ መሆናቸው የተገለፀ 17 ስደተኞች በተያዙበት ሆቴል ውስጥ በኤቦላ እንደተያዘ የሚጠረጠር ቢያንስ አንድ ሰው ተገልሎ እንደሚገኝ የተጠራዦቹ ጠበቆች ተናገሩ። ማላዊ 38 ሺህ ዜጎቿን በአንድ ወር ውስጥ ከደቡብ አፍሪቃ ወደ ሀገራቸው መመለሷን ዛሬ አስታውቃለች። ስድስት የማላዊ ዜጎች መንገድ ላይ ታመው ሞተዋል። የጀርመን የእግር ኳስ ፌደሬሽን በምህጻሩ DFB ፕሬዝዳንት እና ምክትላቸው ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን አስልጣኝነት ከታጩት ከዩርገን ክሎፕ ጋር ለመነጋገር ዛሬ ወደ ኒውዮርክ ተጓዙ።

  • July 9 · 9 min

    የሐሙስ ሐምሌ 2 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    ናሜይ፥ ሩስያ እና የሣኅል ቀጠና አገራት ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ሊያጠናክሩ ነው ፤ አንካራ፥ የኔቶ ጉባኤ በተሳታፊዎች ስምምነት ተጠናቀቀ፤ቤርሊን፥ ራኄ መንግሥት ፍሪደሪሽ ሜርስ ትናንት የተጠናቀቀው ኔቶ ጉባኤ ከጠበቁት በላይ መኾኑን ተናገሩ፤ ቴሕራን፥ ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ ጥቃት እየተሰናዘሩ ነው፤ ማሽሐድ፥የቀድሞዉ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻምኔይ ተቀበሩ፤ ሞሮኮ እና ፈረንሣይ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ፍልሚያ

  • July 8 · 10 min

    የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 01 ቀን 2018 ዓም ረቡዕ

    አርስተ ዜና፤ የደቡብ አፍሪቃ ፖሊስና ወታደራዊ ኃይል በጆሃንስበርግ አቅራቢያ በሕገ-ወጥ የማዕድን ቁፋሮ ሥራዎች ላይ ባደረጉት ከፍተኛ ዘመቻ ከ200 በላይ ሰዎችን አሰሩ። በደቡብ አፍሪቃ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን መካከል ህጋዊ ወረቅት የሌላቸዉ ስለመያዝ አለመያዛቸዉ እስካሁን የወጣ ግልፅ መረጃ የለም።-የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኔቶ ስብሰባ አንካራ ተገኝተዋል። ትራምፕ ድርጅቱ ባሳየዉን ወታደራዊ ኤግዚቢሽን የተደሰቱ አይመስልም። የአውሮጳ ህብረት ሀገራት ኔቶን ለማጠናከር የሚያደርጉትን ጥረትና የኢራን ጦርነት ለመቀላቀል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ትራምፕ በተደጋጋሚ ተችተዋል።

  • July 7 · 11 min

    የማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    አ.አ፥ ጠ/ሚ ዐቢይ ስለ ሕገ መንግሥቱ ተናገሩ፤ ናይሮቢ፥ የኬንያ ፖሊስ የመታሰቢያ ሰልፍ ከለከለ፤ ​​​​​​​ኪንሻሳ፥ የኢቦላ ወረርሺኝ በኮንጎ መዛመቱን እንደቀጠለ ነው፤ ደማስቆስ፥ ሶሪያ ውስጥ በፈረንሣይ ፕሬዚደንት ጉብኝት ወቅት በደረሰ ፍንዳታ 18 ሰዎች ቆሰሉ፤ ፓሪስ፥ ፈረንሣይ እና ሶሪያ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ፤ አትላንታ፥ ወደ ሩብ ፍጻሜ ለመግባት የመጨረሺያ ግጥሚያዎች

  • July 6 · 12 min

    DW Amharic የሰኔ 29 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    የትግራይ ክልል ባለሥልጣናት የ15 ዓመት አዳጊዎችን ጨምሮ ሲቪል ሰዎችን እያፈኑ በግዳጅ ለውትድርና በመመልመል ላይ እንደሚገኙ ሒውማን ራይት ዎች ወነጀለ። በሱዳን እየተካሔደ በሚገኘው ጦርነት በስድስት ወራት ብቻ 330 ሕጻናት መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት አስታወቀ። ሐማስ የጋዛን መንግሥታዊ መዋቅር መፍረሱን አስታወቀ። የዩክሬን ጦር ኦምስክ በተባለ ግዙፉ የሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ጥቃት ፈጸመ። ለጀርመን ለሚቀጥለው ዓመት የ555.4 ቢሊዮን ዩሮ ረቂቅ በጀት ጸደቀ። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ከኢራን ጋር ከሥምምነት ላይ ካልደረሰች አገራቸው የጀመረችውን ጦርነት "እንጨርሰዋለን" ሲሉ ዛቱ

  • July 5 · 7 min

    DW Amharic-የሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የዓለም ዜና

    በዛሬው የዓለም ዜና በቀይ ባሕር ትቀዝፍ የነበረች አንዲት ዕቃ ጫኝ መርከብ በየመን ሁዴይዳ የባሕር ክልል አካባቢ ጥቃት ተፈፀመባት መባሉን፣ እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ በሂዝቦላህ ላይ የምታካሂደውን ዘመቻ አጠናክራ እንደምትቀጥል መግለጿን፣በእስራኤል እስር ቤት ውስጥ የሚገኙት የጋዛ ሆስፒታል ዳይሬክተር ህይወታቸው አደጋ ላይ ወድቋል መባሉን፣ ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የአያቶላህ አሊ ካማኔይ የሀዘን ሥነ ሥርዓት ላይ ልጆቻቸው እና ከፍተኛ የኢራን ባለስልጣናት መገኘታቸውን እንዲሁም ትራምፕ በአሜሪካ 250ኛ ዓመት የነፃነት በዓል ባደረጉት ንግግር የሀገር ፍቅርን ከፓርቲ ፖለቲካ ጋር ቀላቅለዋል በሚል መተቸታቸውን አካቷል።

  • July 4 · 10 min

    የሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የዓለም ዜና

    በዛሬው የዓለም ዜና ፤ የትግራይ ክልል አሁን ያለበት ሁኔታ አሳስቦኛል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መግለፁን፣የአውሮፓ እና የአሜሪካ መሪዎች ስደተኞችን ለመጠበቅ እና ለማዋሃድ የበለጠ እንዲሰሩ የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳሥ ማሳሰባቸውን፣ኢራን ለሟቹ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊካሜኒ ብሄራዊ የሽኝት ሥነ ስርዓት ዛሬ በይፋ መጀመሯን፣ጀርመን፤ ቤጂንግ የሩሲያ ወታደሮችን ማሰልጠኗን የሚያሳዩ ዘገባዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ቻይናን ማስጠንቀቋን፣አማራጭ ለጀርመን የተባለው መጤ ጠል ፓርቲ ዛሬ መሪዎቹን መምረጡን እንዲሁም ዶናልድ ትራምፕ ለ11 ተከሳሾች ይቅርታ ማድረጋቸውን የሚያስቃኙ ዜናዎች ተካተዋል።

  • July 3 · 11 min

    የሰኔ 26 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    -በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዘይሴ ወረዳ የመንግሥት ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸዉን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አስታወቀ።---የቀድሞዉ የኢራን ላዕላይ መሪ አ,ያቶላሕ ዓሊ ኻምኔይ አስከሬን የሽኝት ሥርዓት ዛሬ ቴሕራን ዉስጥ ተጀመረ።ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል ኢራን ላይ ጦርነት በከፈቱበት ዕለት ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ የተገደሉት ኻምኔይ ኢራንን ለ37 ዓመት መርተዋል።86 ዓመታቸዉ ነበር።--ሐሙስ ይቀበራሉ።-የጀርመን የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዩሊያን ናግልስ ማን በከፍተኛ ግፊት ሥልጣኑን ለቀቀ።

  • July 2 · 11 min

    የሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ኮሬ ዞን ተማሪዎች እስካሁን የዓመቱን የማጠቃለያ ፈተና እንዳልተፈተኑ ወላጆች ገለጹ። መምህራኑ «መንግሥት የኑሮ ውድነትን ለመደጎም ያደረገው ውዝፍ የደመወዝ ጭማሪ በተሟላ ሁኔታ አልተከፈለንም» በሚል ወደ ትምህርት ቤት አልሄዱም ተብሏል። በሰሜናዊ ናይጀሪያ ማለቂያ ባጣው ግጭት ምክንያት ታይቶ የማይታወቅ ረሀብ መከሰቱን ዛሬ የተመድ አስታወቀ። የኬንያ ፍርድ ቤት በስምንት ተማሪዎች ላይ የግድያ ክስ መሰረተ። ዛሬ ማለዳ ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 21 ሰዎች መገደላቸውን የከተማዋ ከንቲባ አመለከቱ። 86 ሰዎችም ተጎድተዋል።

  • July 1 · 9 min

    የሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    የሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. አርእስተ ዜና አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የሱዳኑን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በምህጻሩ RSFን በሰብዓዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎችና በዘር ማጥፋት ወንጀል ከሰሰ ። ትውልደ-ኢትዮጵያዊቷ ሶሻል ዴሞክራት ሜላት ኪሮስ ትናንት ማክሰኞ በአሜሪካ በዴንቨር አካባቢ የተካሄደውን ምርጫ አሸነፉ። ሜላት ኪሮስ ለ15 ጊዜ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑትን ዲያና ደጌትን ነew ያሸነፉት ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን በቀጠር ዋና ከተማ ዶሀ ዛሬ ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግር መጀመራቸው ተሰምቷል ።

  • June 30 · 11 min

    የሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    የተመድ የኢቦላ ወረርሽኝ አፍሪቃን እስከ 3,6 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ያስወጣታል አለ። የኬንያ ፖሊስ በዛሬው ዕለት እገታን በመቃወም አደባባይ የወጡ ናቸው በተባሉ ሰዎች ላይ ጥይት ተኩሶ አንድ ሰው መግለደሉን እማኞች አመለከቱ። ሁለት ሰዎችም በጥይት ተጎድተዋል። የተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በሱዳን አል ኦቢድ ጉዳይ አስቸኳይ ክርክር ሊያካሂድ መሆኑ ተገለጸ። በተጠቀሰችው ከተማ ዙሪያ የፈጥኖ ደራሹና ደጋፊዎቹ ኃይሎች መከማቸታቸው ስጋት አስከትሏል። ኢራን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በመጪዎቹ ቀናት የመገናኘት እቅድ የለኝም አለች። ሁለት የአሜሪካ ልዑካን በኢራን ጉዳይ ለመነጋገር ዛሬ ቀጠር መግባታቸው ተዘግቧል።

  • June 29 · 9 min

    DW Amharic የሰኔ 22 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊያ ፕሬዝደንት ሐሰን ሼክ ማሕሙድ ተገናኙ። ለ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎች ሞባይል ስልክ፣ ቅንጡ የእጅ ሰዓቶችና ማዳመጫዎች ወደ መፈተኛ ክፍል ይዘው መግባት ተከለከሉ። ኢትዮጵያ አንድ ቢሊዮን ዶላር የተበደረችበት ቦንድ ባለቤቶችን ከሚወክል ጊዜያዊ ኮሚቴ ጋር የዕዳ አከፋፈል ሽግሽግ ለማድረግ በመርኅ ደረጃ ከሥምምነት መደረሱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። የኬንያ መንግሥት ከአሜሪካ ጋር ሊፈራረም ነው የተባለው የውድ ማዕድናት ፍለጋ “ግልጽነት ይጎድለዋል” የሚል ክስ በፍርድ ቤት ቀረበበት። በጀርመን ኒደር ዛክሰን ግዛት ሽታደ ከተማ በተከፈተ ተኩስ 5 ሰዎች ተገደሉ

  • June 28 · 8 min

    የዕሁድ ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ. ም ፤ የዓለም ዜና

    የዛሬው የዓለም ዜና በሳውዲ አረቢያ እና በፈረንሳይ በደረሰ የሄሊኮፕተር እና የአውሮፕላን አደጋ 25 ሰዎች መሞታቸውን፣ በአውሮጳ በተከሰተው ከፍተኛ የሙቀት ማዕበል በአንድ ሳምንት ብቻ ከ1,300 በላይ ሞት መመዝገቡን፣ ቢያንስ 191 ሚሊዮን ሰዎች ለ35 ዲግሪ ሴልሺየስ ሙቀት ይጋለጣሉ መባሉን፣ ኢራን የአሜሪካን ጥቃት ተከትሎ በባህሬን እና ኩዌት ላይ ጥቃት ማድረሷን እንዲሁም የዩክሬንን ጥቃት ተከትሎ የሩሲያው መሪ የሀገራቸውን ደህንነት ለማረጋገጥ ቃል መግባታቸውን አካቷል።

  • June 27 · 11 min

    የሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

    • በኢትዮጵያ የሚገኘው የአውሮጳ ኅብረት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እያካሔደ ነው የተባለው አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላ የፕሪቶሪያ ግጭት የማቆም ስምምነት በግልጽ የጣሰ ነው ሲል ነቀፈ። • በሱዳን ኤል-ኦቤይድ ከተማ የሚካሄደው ውጊያ ወደ ከፋ ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስጠነቀቀ። • የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት በጎረቤት ሩዋንዳ ላይ በዓለም አቀፉ የወንጀል መዳኛ ፍርድ ቤት (ICJ) ክስ መሰረተች። • ኢራን አሜሪካን "ጦርነቱን ለማቆም የተደረገውን ስምምነት ጥሳለች" ስትል ከሰሰች።

  • June 26 · 10 min

    የዓርብ ሰኔ 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    መቐለ፥ ሕወሓት ለሒውማን ራይትስ ዎች ምላሽ ሰጠ፤ ካርቱም፥ በሱዳን ኤል ኦቤይድ ከተማ ላይ ሌላ ፍጅት እንዳይከሰት አሥግቷል፤ ቱኒስ፥ ኃዋቂዋ ቱኒዚያዊት የ75 ዓመት የመብት ተሟጋች 25 ዓመት እስር ተፈረደባቸው፤ ዋሽንግተን፥ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሔይቲ እና ሶሪያ ዜጎች በገፍ ከአገር እንዲባረሩ የሚያስችል መንገድ ጠረገ፤ ፓሪስ፥ አውሮጳን የመታው የሙቀት ማእበል እንደበረታ ነው፤ ካራካስ፥ ከብርቱው ርእደ መሬት የተረፉትን ለማዳን ርብርቡ ቀጥሏል፤ ኒው ጄርዚ፥ የዓለም ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ እየተገባደደ ነው