የዓለም ዜና

የሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

July 15 · 10 min · 11.3 MB
0:00-10:13

Streams straight from the publisher. podnod never proxies or re-hosts episode audio.

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ተጀምሯል። ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ « ለእኔ ሳይሆን ለእኛ፣ ለኢትዮጵያ ማለት ከቻልን ምክክሩ ፍሬያማ ይሆናል በማለት ለጉባኤተኞቹ ጥሪ አቅርበዋል።

ወደቦትስዋና ለመሻገር የሞከሩ 10 ኢትዮጵያውያን የተሳፈሩባት ታንኳ ተገልብጣ ሳይሰጥሙ እንዳልቀረ የዛምብያ ባለሥልጣናት ዛሬ አስታወቁ። በታንኳዋ ተሳፍረው ከነበሩት 15 ኢትዮጵያውያን አስሩ ሰጥመዋል ተብሎ እንደሚታመን የተናገረው ፖሊስ ሦስት ደግሞ የደረሱበት እንዳልታወቀ ገልጿል። ከመካከላቸው በህይወት የተረፉትን ሁለቱን ፖሊስ አስሯቸዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ እና የኢራን ጥቃትና የአጸፋ ጥቃት ዛሬም ቀጥሏል።