
0:00-11:41
Streams straight from the publisher. podnod never proxies or re-hosts episode audio.
በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ኮሬ ዞን ተማሪዎች እስካሁን የዓመቱን የማጠቃለያ ፈተና እንዳልተፈተኑ ወላጆች ገለጹ። መምህራኑ «መንግሥት የኑሮ ውድነትን ለመደጎም ያደረገው ውዝፍ የደመወዝ ጭማሪ በተሟላ ሁኔታ አልተከፈለንም» በሚል ወደ ትምህርት ቤት አልሄዱም ተብሏል።
በሰሜናዊ ናይጀሪያ ማለቂያ ባጣው ግጭት ምክንያት ታይቶ የማይታወቅ ረሀብ መከሰቱን ዛሬ የተመድ አስታወቀ።
የኬንያ ፍርድ ቤት በስምንት ተማሪዎች ላይ የግድያ ክስ መሰረተ።
ዛሬ ማለዳ ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 21 ሰዎች መገደላቸውን የከተማዋ ከንቲባ አመለከቱ። 86 ሰዎችም ተጎድተዋል።
No links were found in this episode’s notes.