Artwork for የዓለም ዜና
News

የዓለም ዜና

DW

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።

  • 100 episodes
  • Updated Monday

Episodes100

  • June 5 · 10 min

    የዓለም ዜና፤ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም አርብ

    አርስተ ዜና-አሜሪካ በኩባ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ አሳረፈች። --ቅድሚያ ለሰብአዊ መብት የተባለ አገር በቀል የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ በትግራይ እየተካሄደ ነው ባለው አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላን እንዲያወግዝ እና እንዲያስቆም ጥሪ አቀረበ።--በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቡርጂ እና ጌዴኦ ዞኖች ምርጫ ሲያጭበረብሩ የተገኙ ከስድስት እስከ አሥር ወር እሥራት ተቀጡ ፡፡--የቀድሞ የአዲስ አበባን ከንቲ አምባሳደር ዓሊ አብዶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።--የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ከአራት ዓመታት በላይ የዘለቀው ጦርነት እንዲያበቃ ስምምነት ላይ ለመድረስ ለፑቲን ግልፅ ደብዳቤ ፃፉ።

  • June 4 · 11 min

    የግንቦት 27 ቀን 2018፤ ዓለም ዜና

    በዛሬው የዓለም ዜና ተቃዋሚው የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በክልሉ ምርጫ«የማጭበርበር ተግባራት ተፈጽሟል» ሲል ቅሬታ ማቅረቡን።የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ)በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ የተከሰተዉ ሁከት በጥልቅ እንዳሳሰበው ማስታወቁ።በዓለም ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ችላ ተብለዋል ሲል አንድ የእርዳታ ድርጅት መግለጹን።ሊባኖስ፤ የእስራኤል የድሮን ጥቃቶች መቀጠላቸውን መግለጿ።ኩዌት የኢራን ድሮን አውሮፕላን ማረፊያዋን መምታቱን ማስታወቋን።የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ሀገሪቱ በኢራን የምታደርገውን ወታደራዊ እርምጃ ለማስቆም የቀረበውን ውሳኔ መደገፋቸውን የሚያስቃኙ ዜናዎች የሚሉት ተካተዋል።

  • June 3 · 11 min

    የግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    የግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን እየሰፋ መጣ ያሉትን ጥቃት የመንግሥት የፀጥታ አካላት ያላቸውን መዋቅር ተጠቅመው እንዲያስቆሙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ጠየቁ። በኢትዮጵያ የአውሮጳ ኅብረት ልዑክ እና በአዲስ አበባ የሚገኙ የኅብረቱ አባል ሃገራት ኤምባሲዎች ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ምርጫ ያልተካሔደባቸው የምርጫ ክልሎች ድምፅ የመስጠት «ዕድል ይሰጣቸዋል» የሚል ተስፋ እንዳላቸው አስታወቁ። ዴሞክራቲክ ኮንጎ ውስጥ በኢቦላ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 343 ደረሰ። ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት ቀጥላለች።

  • June 2 · 11 min

    የዓለም ዜና፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ማክሰኞ

    -አርሰተ ዜናዎች--ሩሲያ በዩክሬን ላይ በድጋሚ በሰነዘረችዉ ከፍተኛ ጥቃት ቢያንስ አስር ሰዎች ተገደሉ ከ100 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆሰሉ።-በኢትዮጵያ የተካሄደው የሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ የድምፅ ቆጠራ ውጤት፣ በምርጫ ጣቢያዎች እየተለጠፈ ይገኛል።--በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ሀገረ ስብከት በአስኮ ወረዳ በሺርካ ወረዳና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 13 ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያኖች መገደላቸውን ሀገር ስብከቱ አመለከተ። የመቶ አንድ ዓመት እድሜ እንደነበረው የተገለጸው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንም ሙሉ በሙሉ በእሳት መጋየቱ ተነግሯል።

  • May 31 · 8 min

    DW Amharic የግንቦት 23 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    የጋምቤላ ክልል ፖሊስ “የተለየ የይለፍ ፈቃድ ካልተሰጠ በቀር” ማንኛውም ተሽከርካሪ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት መንቀሳቀስ እንደማይችል አስታወቀ። በምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አምስት ሕሙማን ከኢቦላ ማገገማቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድኃኖም ተናገሩ። ኢራን ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው ድርድር የኑክሌር የጦር መሣሪያ ላለመስራት መስማማቷን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገለጹ። የኢራን ዋና ተደራዳሪ ሞሐመድ ባግኸር ጋሊባፍ ግን “የኢራናውያን መብቶች መከበራቸውን ሳናረጋግጥ አንዳች ሥምምነት አናጸድቅም” ብለዋል።

  • May 30 · 9 min

    የግንቦት 22 ቀን 2018 ፤የዓለም ዜና

    የዛሬው የዓለም ዜና፤የአማራ ፋኖ የጣለው የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ገደብ የምርጫ ሥራዉን ስለማስተጎጎሉ የደረሰው መረጃ እንደሌለ ምርጫ ቤርድ ማስታወቁ፣የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የኢቦላ ወረርሽን ወደተቀሰቀሰባት ዲሞክራቲክ ኮንጎ ማምራታቸውን፣ እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ ነዋሪዎች አካባቢውን እንዲለቁ ትዕዛዝ መስጠቷን፣ በጀርመን የሙኒክ አውሮፕላን ማረፊያ አጠራጣሪ ድሮን መታየቱን ተከትሎ ለአጭር ጊዜ በረራ መቋረጡን አሜሪካ ስምምነት ላይ ካልደረሰ በኢራን ጦርነቱን እንደገና ለመጀመር ዝግጁ መሆኗን መግለጿን፣እንዲሁምሩሲያ፤ በአርሜኒያ የሚገኙ አምሳደሯን መጥራቷን አካቷል።

  • May 29 · 11 min

    የግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    ከአማራ ክልል መንገደኞችን ጭኖ ትናንት ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ አውቶብስ ላይ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ተሰማ። ማዕከላዊ ኬንያ ውስጥ በሚገኘው የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት የተነሳውን እሳት በመለኮስ የተጠረጠሩ ስምንት ተማሪዎች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ። የኬንያ ፍርድ ቤት በሀገሪቱ በኤቦላ ተሐዋሲ ለተያዙ የአሜሪካ ዜጎች አግልሎ ማቆያ የማዘጋጀት እቅድን በጊዜያዊነት አገደ። ኢራን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ለገባችበት ውዝግብ ለታሰበው የሰላም ስምምነት ከቃል ይልቅ ተግባር እንደምትፈልግ አስታወቀች።

  • May 28 · 10 min

    DW Amharic የግንቦት 20 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ በጥሞና ወቅት “ፕሮጀክት ማስጀመር እና ማስመረቅ” ከለከለ። ክልከላው የምርጫውን ተዓማኒነት ለማረጋገጥ ያግዛል በተባለው የጥሞና ጊዜ ከማይደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የተካተተ ነው። ከኢትዮጵያ መንግሥት የሚዋጋው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ከነገ ጀምሮ በአማራ ክልል “ለተከታታይ አምስት ቀናት ከአንቡላንሶች በስተቀር ሁሉም መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ መደረጋቸውን” አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግሥት አገሪቱ አንድ ቢሊዮን ዶላር የተበደረችበት ቦንድ ባለቤቶችን ከሚወክል ጊዜያዊ ኮሚቴ ጋር ያደረገው ውይይት ውጤታማ ሳይሆን መቅረቱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

  • May 27 · 9 min

    የረቡዕ ግንቦት 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    አ.አ፥ ለቀጣዩ ምርጫ ሥራ ዝግ እንደሚኾን ምርጫ ቦርድ ዐሳወቀ፤ አ.አ፥ 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በመላ ኢትዮጵያ ተከበረ፤ ጆሐንስበርግ፥ የጋና መንግሥት ዜጎቹን መጤ ጠል ሥጋት ካጠላባት ደቡብ አፍሪቃ ወደ አገራቸው እየመለሰ ነው፤ ዋሽንግተን፥ ካናዳ እና ባሐማ ከኤቦላ ጋር የተገናኘ የጉዞ ክልከላ ተግባራዊ አደረጉ፤ ናይሮቢ፥ ካናዳ እና ባሐማ ከኤቦላ ጋር የተገናኘ የጉዞ ክልከላ ተግባራዊ አደረጉ፤ ጋዛ፥እሥራኤል አዲስ የተሾሙ የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ አዛዥን መግደሏን ዐሳወቀች፤

  • May 26 · 10 min

    የግንቦት 18 ቀን 2018 ዓም የዓለም ዜና

    የግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና በሱዳኑ ጦርነት ከፈጥኖ ደራሹ ኃይል በምህጻሩ RSF ጎን ተሰልፈው የሚዋጉ ኮሎምብያውያን የግል ቅጥረኛ ወታደሮችን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ታሰለጥናለች ሲል ሂዩመን ራይትስ ዋች አስታወቀ ። በኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እጎ ዩጋንዳ ዉስጥ ተጨማሪ ሰዎች በኢቦላ ተሕዋሲ መያዛቸዉን የሁለቱ ሐገራት የጤና ባለሥልጣናት አስታወቁ። ኢራን፣ ዩናይትድ ስቴትስ ትናንት የፈጸመችባትን የአየር ድብደባ አወገዘች። ድብደባዎቹን የተኩስ አቁሙን የጣሰ ሲል ያወገዘው የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት፣ ጥቃቶቹ ለሚያስከትሉት መዘዞች ሁሉ ዋሽንግተን ሃላፊነቱን እንደምትወስድ አስጠንቅቋል።

  • May 25 · 10 min

    የግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    መገናኛ ብዙኃን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በመንግሥት ቁጥጥር ስር በሆነበት፤ አመጽና ዛቻን በመጋፈጥ፤ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚካሄደው ምርጫ እንደሚሳተፉ ተዘገበ። ዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልእኮ የወታደሮች ቁጥር በመቀሱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አንድ ጥናት አመለከቱ። ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነቱን ለማስቆም ከአሜሪካ ጋር የምታካሄደው ድርድር መሻሻሎች ቢኖሩትም ስምምነት ላይ ገና አልተደረሰም አለች። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ከኢራን ጋር የሚደረገው ስምምነት ወይ ታላቅና ትርጉም ያለው ይሆናል ወይ ደግሞ ስምምነት አይኖርም ብለዋል።

  • May 24 · 7 min

    የግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

    • በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ የሟቾች ቁጥር 204 ደረሰ። ኢትዮጵያን ጨምሮ 10 የአፍሪካ ሀገራት ወረርሽኙ አስግቷቸዋል። • አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱን ለማቆም የሚያስችላቸው ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረባቸው ተሰማ። • ሩሲያ ዛሬ ሌሊት በዩክሬን መጠነ-ሰፊ የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃት “ኦሬሽኒክ” የተሰኘውን የሃይፐርሶኒክ ባሊስቲክ ሚሳኤል • በፓኪስታን በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት የ23 ሰዎች ህይወት አለፈ። • ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች ዛሬ ደቡብ አፍሪቃ ኬፕታውን ውስጥ የተደረገውን የማራቶን ሩጫ የቦታውን ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር አሸነፉ ።

  • May 23 · 10 min

    የግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና ኡጋንዳ በተጨማሪ 10 የአፍሪካ ሐገራት የኢቦላ ቫይረስ ሥርጭት እንደሚያሰጋቸው የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ድርጅት አስታወቀ። ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ ዳግም ጦርነት የምታውጅ ከሆነ ብርቱ አጸፋዊ ምላሽ እንደምትሰጥ ኢራን አስጠነቀቀች። በሰሜን ቻይና በምትገኝ የሻንዚ ግዛት በአንድ የከሰል ማዕድን ማውጫ ትላንት ባጋጠመ ፍንዳታ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 90 መድረሱን ተሰማ። ዩክሬይን በሩስያ ቁጥጥር ሥር በሚገኘው እና የቀድሞ ግዛቷ በነበረው ሉጋንስክ ከተማ ፈጸመችው በተባለ የድሮን ጥቃት 18 ሰላማዊ ሰዎች ሲሞቱ 48 መቁሰላቸውን የአካባቢው የሩስያ ገዢ አስታወቁ።

  • May 22 · 12 min

    የዓለም ዜና፤ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም አርብ

    አርስተ ዜና -የደቡብ አፍሪቃ ባለስልጣናት ተባብሶ የቀጠለዉን ጥቁር የውጭ ዜጋ ጥላቻን ተከትሎ ጥቃትን በመፍራት ደርባን በሚገኘ አንድ የቤተክርስቲያን ማእከል ዉስጥ ከለላ የጠየቁ አፍሪቃዉያን ከማዕከሉ አስወጡ። ኢትዮጵያዉያንም ይገኙበታል።-ህንድና የአፍሪቃ ህብረት በሚቀጥለው ሳምንት በኒው ደልሂ ሊያካሂዱት የነበረው የመሪዎች ጉባዔ በኮንጎ በተቀሰቀሰዉ የኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ። -የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ ፈረንሳይ በቅኝ ግዛቶቿ የነበረውን ባርነት ለመቆጣጠር ያገለገሉትን ያረጁ ህግጋቶች እንድታስወግድ እንደሚፈልጉ ተናገሩ። ሕግጋቱ አገራቸዉ ዛሬ ከምትላቸው እሴቶች ጋር አይጣጣሙም ብለዋል።

  • May 21 · 10 min

    የግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    የግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ለመንግሥት አቅርቦት የነበረው ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ ባለማግኘቱ በምርጫው ተሳትፎው እጅግ የተቀዛቀዘ እንዲሆን ማድረጉን አስታወቀ ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ በክልሉ የ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ከታቀደው አንድ ወር ቀደም ብሎ እንደሚያበቃ አስታወቀ። ባለፉት 3 ሳምንታት ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ዩጋንዳ ወይም ደቡብ ሱዳን የነበሩ አሜሪካውያን ጠለቅ ላለ ምርመራ ፣በዋሽንግተን ዳላስ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ብቻ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲገቡ የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳሰበ ።

  • May 20 · 11 min

    የግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

    የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ «አለአግባብ ከምርጫው ተሳትፎ አግልሎኛል» ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ላይ ክስ መሠረተ። ምርጫ ቦርድ በበኩሉ የዕጩዎችን ምዝገባ አጠናቅቄ የድምፅ መስጫ ወረቀት ኅትመት ጀምሬያለሁ ይላል። የአውሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ከጎርጎሪዮሳዊው 2024 ዓ,ም ጀምሮ ኢትዮጵያ ላይ ጥሎት የቆየው የቪዛ ገደብ መነሳቱን አስታወቀ። የዓለም የጤና ድርጅት በኤቦላ መሞታቸው የተጠረጠረ ሰዎች ቁጥር 139 መድረሱን ዛሬ አስታወቀ። በተሐዋሲው መያዛቸው የተጠረጠረም 600 ደርሰዋል። ሩሲያና ቻይና ለዩክሬን ጦርነት መንስኤ የሆኑ መሠረታዊ ነገሮች እንዲወገዱ ጥሪ አቀረቡ። በኢራን ላይ የሚደርሰውን ጥቃትም ኮነኑ።

  • May 19 · 10 min

    የማክሰኞ ግንቦት 11 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

    መቐለ፥ «የትግራይ የሰላምና ለውጥ ምክር ቤት» ምሥረታን ሕወሓት አጣጣለ፤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዐቃቢያነ-ሕግጋት ከፊል የሥራ ማቆም አደረጉ፤ ኪንሻሳ፥ የኢቦላ ወረርሺኝ አኅጉራዊ የጤና ሥጋት መኾኑ ታወጀ፤ ቤርሊን፥ አሜሪካዊ የኮሮና ታማሚ ጀርመን ለልዩ ኅክምና ተወሰደ፤ ሞስኮ፦ ቤላሩስ ከሩስያ ጋር የኑክሊየር ጦር መሣሪያን የሚያካትት ወታደራዊ ልምምድ መጀመሯን ይፋ አደረገች፤ ካይሮ፥ የአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያ ድልድል ይፋ ኾነ

  • May 18 · 10 min

    የዓለም ዜና፤ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ

    አርስተ ዜና፦ በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ የተባለ ጭማሪ በመደረጉ አገር አቀፍ የትራንስፖርት አድማ ተቀሰቀሰ። ናይሮቢን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ ተቃዉሞዉ ቀጥሏል። -ለአፍሪቃ ቀንድ ሰላም እንዲሰሩ በድጋሚ የተሾሙት የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ፣ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል ያለውን ልዩነት በበለጠ ብልሃትና ስልታዊ አካሄድ መፍታት እንደሚገባቸው ተመለከተ።-የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ቴህራን ላይ ጫና በማሳረፍ ስምምነት ላይ ካልተደረሰ ኢራን ትወድማለች" ሲሉ በድጋሚ ዛቱ።-በፈረንጆቹ 2025 ዓመት በዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር የሞት ቅጣት መፈፀሙን፤ አምነስቲ አስታወቀ።

  • May 17 · 7 min

    DW Amharic- የግንቦት 09 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    በዛሬው የዓለም ዜና የዓለም ጤና ድርጅት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በt,ከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት ዓለም አቀፍ የአስኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን፣በናይጄሪያ ወታደራዊ ትምህርት ቤት ላይ በተፈፀመ የአክራሪዎች ጥቃት 17 የፖሊስ ሰልጣኞች መገደላቸውን፣በዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ የኒኩሌር ማዕከል ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት በማዕከሉ ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን፣ አሜሪካ ለኢራን የድርድር ሀሳብ በሰጠችው ምላሽ ላይ ምንም አይነት ተጨባጭ የስምምነት ሀሳብ የለውም ሲሉ የኢራን መገናኛ ዘዴዎች መግለፃቸውን እንዲሁም የሰሜን ኮሪያ የሴቶች የእግር ኳስ ቡድን በደቡብ ኮሪያ ጉብኝት ማድረጉን አካቷል።

  • May 16 · 8 min

    DW Amharic የግንቦት 08 ቀን 2018 የዓለም ዜና

    ኤርትራ እና ግብጽ የባሕር ትራንስፖርት የትብብር ሥምምነት ዛሬ ቅዳሜ በአስመራ ተፈራረሙ። ሥምምነቱ የተፈረመው የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ በተገኙበት ነው። በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኢቱሪ ግዛት በኢቦላ ወረርሽኝ ቢያንስ 80 ሰዎች ሞቱ። የቦኮ ሐራም አባላት ሳይሆኑ አይቀሩም የተባሉ ታጣቂዎች በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ቦርኖ ግዛት ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት ከፈጸሙት ጥቃት በኋላ ቢያንስ 42 ልጆች ደብዛቸው መጥፋቱን የአካባቢው ተመራጭ ተናገሩ። የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ አዛዥ ኢዚዲን አል-ሐዳድ ተገደሉ።