የዓለም ዜና

DW Amharic የሐምሌ 12 ቀን 2018 የዓለም ዜና

July 19 · 7 min · 9.1 MB
0:00-7:55

Streams straight from the publisher. podnod never proxies or re-hosts episode audio.

በሶማሌ ክልል ቀብሪ በያሕ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ። ለ2019 የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት 704 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ። በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ምዕራባዊ ክፍሎች፤ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልና በጋምቤላ ክልል በተወሰኑ አካባቢዎች በሚጥል ከባድ ዝናብ ምክንያት የጎርፍ መጥለቅለቅ ሊከሰት እንደሚችል የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስጠነቀቀ። የታንዛኒያ ሰንደቅ የሚያውለበልብ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ከየመን የባሕር ዳርቻ በሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎች ታገተ። አሜሪካ ሁለት ወታደሮቿ በዮርዳኖስ ከተገደሉ በኋላ ኢራንን “ለመቅጣት” አዲስ ዙር የለሊት የአየር ላይ ድብደባ ፈጸመች።