Artwork for ዜና መጽሔት
News

ዜና መጽሔት

DW

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።

  • 100 episodes
  • Updated Yesterday

Episodes100

  • July 6 · 14 min

    DW Amharic የሰኔ 29 ቀን 2018 ዜና መጽሔት

    በአፍሪቃ ቀንድ እየጨመረ የመጣው የጦርነት ስጋት፣ የፀጥታ ሥጋት ያጋጠመው የጋሞ ዞን ዛይሴ አካባቢ፣ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ያልተቀመጠዉ የትግራይ ክልል ቅሬታ

  • July 3 · 22 min

    የሰኔ 26 ቀን 2018 የዜና መጽሔት

    እቅዱን አሳክቷል የተባለው የኢትዮጵያ የቡና ገቢ ፣ በአሜሪካ የትግራይ ማኅበረሰብ አባላት፣ስለትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ የሰጡት አስተያየት ፣በድሬደዋ የተማሪ ህፃናት ምገባን በተደራጃ መንገድ ማከናወን ያስችላል የተባለ ፕሮጀክት በይፋ መጀመሩ እንዲሁም የቀድሞ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ አስከሬን ሽኝት የተሰኙት ርዕሶች ይተነተናሉ።

  • July 2 · 26 min

    የሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት

    የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ታጣቂዎች 13 ሰዎች መግደላቸዉን የሚቃኝ ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ የኮሬ ዞን አስተማሪዎች ተማሪዎችን ላለመፈተን ማደማቸዉን ከዞኑ አስተዳደር መልስ ጋር ያሰባጠረ ዘገባም አለዉ።የአዉሮጳ የሙቀት መጠን ማየልና የፖለቲካዊ መርሕ ለዉጥ ጥያቄ፣ የቻይና ኮሚንስት ፓርቲ 105ኛ ዓመት በአል፣ የዓለም የእግር ኳስ ግጥሚያ የአፍሪቃ ቡድናት ሽንፈት ያልናቸዉንም ርዕሶች ያስተነትናል።

  • July 1 · 18 min

    የሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት

    የዜና መጽሔት፤ አዲሱ የመኖሪያ ቤት የኪራይ ዋጋ ጥናት፤ በጋምቤላ ክልል ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴዎች ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ስለሚኖራቸው ሚና፤ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና መጀመሩ እንዲሁም የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እዚያ ስለሚወለዱ ልጆች ዜግነት ያሳለፈው ውሳኔን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።

  • June 30 · 19 min

    የሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት

    የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የኤርትራ የወደፊት ኅልዉና የፕሬዝደንቷ አገዛዝ ያልነዉን ርዕሥ ያስቀድማል። ዜና መፅሔቱ አዲስ አበባ ዉስጥ በተዘዋዋሪ አዉቶብሶች የዲጅታል የሕዝብ አገልግሎት መሰጠቱ፣ የደቡብ አፍሪቃ መጤ ጠል ቡድናት በከፈቱት ዘመቻ ላይ ሊነጋገር የነበረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ስብሰባ መራዘምና የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን የሚቃኙ ዘገቦችና ቃለ ምልልስን አካቷል።

  • June 29 · 19 min

    DW Amharic የሰኔ 22 ቀን 2018 ዜና መጽሔት

    የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ የኢትዮጵያ ጉብኝት፣ በትግራይ የወጣቶች አፈሳ ቀጥሏል መባሉና የአውሮፓ ህብረት ማስጠንቀቂያ፣ የቀነ ገደቡ መጠናቀቅ እና የፍልሰተኞች ሥጋት በደቡብ አፍሪካ

  • June 26 · 25 min

    የዓርብ ሰኔ 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት

    ዜናዉን የሚለጥቀዉ የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አዲስ የደነገገዉን ሕግ እንዲሽር ሑማን ራይትስ ዋች ያቀረበዉን ጥያቄ ህወሃት ዉድማድረጉን የሚተነትነዉን ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ፣ የጋቤላ ብልፅግና ፓርቲ ፅሕፈት ቤት ከተቃዋሚዎች ጋር ተባብሮ ለመሥራት ቃል መግባቱ፣ ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጥቃት ይደርስብናል የሚለዉ ሥጋታቸዉ መናሩ፣ የመረጃ ጥቅም፣ የአፍሪቃ አቅምና ዝግጅት፣ እንዲሁም የዓለም የእግር ኳስ የዋንጫ ግጥሚያን የሚቃኙ ዘገቦችና አጭር ዉይይቶች አሉት።

  • June 25 · 24 min

    የሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት

    የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለምክክር ጉባኤ የመረጣቸው ስምንቱ አጀንዳዎች፤ በአስተያየት ሰጪዎች ተስፋ እና ሥጋት የተንጸባረቀበት አገራዊ ምክክር፤ የኦሮሚያ ክልሉ ግጭት እና ዘላቂ መፍትሄው፤ የኢቦላ ስርጭትን ለመከላከል የጉዞ እገዳ አስፈላጊ አይደለም ሲል ዐአፍሪካ ሲዲሲ ዐሳወቀ፤ በስፔን ከ200 በላይ ሰዎችን የገደለው የሙቀት ወጀብ በፈረንሣይስ ምን አደረሰ?

  • June 24 · 17 min

    የሰኔ 17 ቀን 2018 የዜና መፅሔት

    በዛሬው የዜና መፅሔታችን 4 ርዕሰጉዳዮች ይደመጣሉ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሦስት የፀጥታ አባላት መገደላቸውን፤ የትግራይ ጊዚያዊ መስተዳደር ያረቀቀው አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመልን እንዲሰርዝ ሂዩማን ራይትስ ዎች መጠየቁን ከተመራጬ መንግስት ምን ይጠበቃል? በሚል መራጮች የሰጡት አስተያየት እንዲሁም የ12 ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን የሚመለከቱ ናቸው በዚሁ ቅደም ተከተል ይደመጣሉ።

  • June 23 · 24 min

    የሰኔ 16 ቀን 2018 የዜና መጽሔት

    የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያ ዉስጥ የተደረገዉን ምርጫ ዉጤት በተመለከተ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሰጡት፣ ድጋፍ፣ ተቃዉሞና ምክርን በሁለት ዘገቦች እንቃኛለን።ከምርጫ ጋር የተያያዘ ነዉ በተባለ ጥራሬ አንድ የቀድሞ ዕጩ መታሰራቸዉን የሚያወሳ ዘገባም ሌላዉ ምርጫነክ ዘገባችን ነዉ።ዜና መፅሔቱ የህወሓት ታጣቂዎች አፋር ክልልን ማጥቃት ሰዎች መግደልና ማቁሰላቸዉንና የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችን መዘዝ የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።

  • June 22 · 17 min

    የሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መፅሔት

    መጽሄተ ዜናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ትናንት እሁድ ይፋ ባደረገው 7ኛ ው ጠቅላላ ሃገራዊ የምርጫ ዉጤት ላይ ያተኩራል። በቅርቡ ከኢትዮጵያ የተባረረችው ፈረሳያዊቷ ጋዜጠኛን አስመልክቶ ቀጣሪዋ ላክሮዋ ጋዜጣ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ያቀረበው ወቀሳም በዝርዝር ከሚደመጡ ዘገባዎቻችን አንዱ ነው።

  • June 20 · 3 min

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ ውጤቶችን ይፋ አደረገ

    ምርጫ ቦርድ ትናንት ዓርብ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ ተጨማሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤቶች እጩ አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ቦርዱ ይፋ ካደረጋቸው ውጤቶች መካከል የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ እንዲሁም የቀድሞ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በግላቸው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበር አሸንፈዋል።

  • June 19 · 23 min

    DW Amharic የሰኔ 12 ቀን 2018 የዜና መጽሔት

    በሰኔ 12 ቀን 2018 የዜና መጽሔት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ “አክራሪ” ባሏቸው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባላትና በቤተሰቦቻቸው ላይ የጣሉትን የቪዛ ገደብ የተመለከቱ ሁለት ዘገባዎች ተካተዋል። የውክልና መቀመጫ ያገኙ ፓርቲዎች ቀጣይ መንገድ፣ ሥመ-ጥሩው የሙዚቃ ባለሙያ አዲስ ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፣ ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰበብ ከአሜሪካ የሚመጣውን ጫና እንዴት ልትይዝ ይገባል? የሚሉ ዘገባዎችም ይቀርባሉ።

  • June 18 · 25 min

    የሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት

    የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያን ወደ ባሕር በር መመለስ በአፍሪካ ቀንድ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና የደህንነት ትብብርን ያጠናክራል መባሉ፤ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች ቁጥር ሻል ብሎ የታየበት የምርጫ ውጤት፤ መሶብ» የሚል መጠሪያ የተሰጠው የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ በጥብቅ የመንግሥት ቁጥጥር የሚመራው የቤት ኪራይና ዳራው፤ እንዲሁም የክረምት ወራት የአየር ጠባይ ሁኔታ ትንበያን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።

  • June 17 · 21 min

    የሰኔ 10 ቀን 2018 የዜና መጽሔት

    አሳሳቢው የጦርነት ስጋት በሰሜን ኢትዮጵያ ፣የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ «የቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ»ን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ፣ ዩናይትድ ስቴትሰና ኢራን ደረሱበት የተባለው ስምምነት አፍሪካን እንዳያዘናጋ ተንታኛች ማሳሰባቸው እንዲሁም ትራምፕን ጨምሮ የቡድን ሰባት አባል ሀገራት መሪዎች ዩክሬንን ለመደገፍ መስማማታቸው የዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ናቸው

  • June 16 · 19 min

    የሰኔ 9ቀን 2018 የዜና መፅሔት

    የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያ ዉስጥ የኑሮ ዉድነት በደሞዝተኞች ላይ ያሳረፈዉን ጫና ችግር የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።በትግራይ ክልል አዲስ የወጣዉ የወታደራዊ አገልግሎት ሕግ ያስከተለዉ ተቃዉሞና ሥጋት፣ ኢትዮጵያዊት ጋዜጠኛ መታሰሯና የአፍሪቃ ሕብረት ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ በተቀጣጠለዉ የዉጪ ጠል ጥቃትና ዛቻ ላይ ሊነጋገር ማቀዱን ዜና መፅሔቱ በየተራ ይተነትናል።

  • June 15 · 16 min

    DW Amharic የሰኔ 08 ቀን 2018 የዜና መጽሔት

    በሰኔ 08 ቀን 2018 የዜና መጽሔት የቱለማ አባገዳ ሥልጣን ሽግግር እና የቀጣዩ አባገዳ ፈተና፣ የኢራን አሜሪካ ስምምነት እንዲሁም የጡት ወተት ባንክ ምንድን ነው? የሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ተካተዋል።

  • June 12 · 23 min

    የሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት

    የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ጥሪ ነዋሪዎች ከአሸናፊው ፓርቲ ምን ይጠብቃሉ ? ሳዑዲ አረቢያ 4 ኢትዮጵያውያንን በሞት ቀጣች፤ 1655 ዜጎች ደግሞ በምህረት እንዲለቀቁ ተደረገ ለአሜሪካዉያን የኤቦላ ማገገምያ ማዕከል ኬንያ ዉስጥ መገንባቱ ያስነሳዉ ተቃዉሞ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረትና ደቡብ ኮሪያ፤ የሰሜን ኮሪይና ቻይና ጉባኤዎች

  • June 11 · 25 min

    የሐሙስ ሰኔ 4 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት

    በዜና መፅሔት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ውጤቶችና እያሳወቀ እና ቅሬታዎችንም እያጣራ መሆኑን መናገሩ፣ ሰቆጣ የተጠለሉ የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጻግምጅ እና አበርገሌ ወረዳዎች ተፈናቃዮች ለረሀብ መጋለጣቸውን መግለፃቸው ፣ -ደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሰቆቃ መቀጠሉ ፣ የኤቦላ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችሉ የቅኝት ስራዎች እንዲጠናከሩ መጠየቁ ፣ ዛሬ በሜክሲኮ የሚጀመረው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የሚያስቃኘን ጉዳዮች ናቸው ። በባህል መድረክ ለህክምና ወደ በጀርመን በመጣበት አጋጣሚ እና የስዕል እግዚቢሽን ያቀረበውን ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላን እንግዳዉ አድርጓል።

  • June 10 · 18 min

    የሰኔ 3 ቀን፣ 2018 የዜና መፅሔት

    ዜናውን የሚከተለው የዜና መጽሔት፣ ጋምቤላ ክልል ዳግም ያገረሸው የፀጥታ ስጋት፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ24 የምርጫ ጣቢያዎችን ውጤት ይፋ ማድረግ መጀመሩ፤ ለመጪው ዓመት ከ2,3 ትሪሊየን በላይ ብር የመንግሥት በጀት መታቀዱ እንዲሁም የዲጂታል ገቢ እና አዲሱ ፈተና የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።