Artwork for ዜና መጽሔት
News

ዜና መጽሔት

DW

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።

  • 100 episodes
  • Updated Monday

Episodes100

  • May 13 · 18 min

    የግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት

    መተከል ዞን ጉባ ወረዳ ከ30 በላይ መንገደኞች በታጣቂዎች መገደላቸዉን የሚያወሳዉን ዘገባ ያስቀድማል።የህወሓት አባላት ናቸዉ የተባሉ ታጣቂዎች ከራያ አለማጣ ከተማ 50 የቤተ-ክሕነት ተማሪዎች ማገታቸዉ ከደሴ ሲዘገብ፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበራት ሕብረት አንዳድ አካባቢ በመራጮች ምዝገባ ሒደት ሕግ መጣሱን አስታዉቋል።ዜና መፅሔቱ የትግራይ ጋዜጠኞች ከክልሉ ወደ ሌላ አካባቢ ለመሔድ መገደዳቸዉን የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።

  • May 12 · 21 min

    የግንቦት 4 ቀን 2018 የዜና መፅሔት

    የዓለም ዜናውን በሚከተለው የዜና መጽሔት፣-በዋግ ኸምራ ዞን የአበርገሌ ወረዳ ተፈናቃዮች አቤቱታ፤ ዓለም አቀፉ የፍልሰኞች ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ፍልሰተኞች በአደገኛው መስመር መጓዛቸውን አላቆሙም ማለቱ፤ የኢትዮጵያ የምርጫ ስርዓት፤ አብላጫ ድምጽ ወይስ ተመጣጣኝ? ፤ የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የስብሰባ ትኩረት እንዲሁም ከመሬት ለአራሹ ትግል እስከ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዘለቁትና ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አቶ ዘገየ አስፋውንም የሚያስታውስ ጥንቅር አካቷል።

  • May 11 · 19 min

    የግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት

    በዜና መፅሄት ጥንቅራችን -ለሰባተኛው ዙር ምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በገንዘብ ድልድል ላይ ያቀረቡት ቅሬታ -የኢኮኖሚ ዕድገት መመዘኛ የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታም ከግምት ማስገባት አለበት መባሉን -የአየር ንብረትን መቋቋም የሚያስችል የግብርና ቴክኖሎጂን የተመለከተ ዓለም አቀፍ ስብሰባ በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ መካሄዱን -የኢራን የሰላም ዕቅድ በአሜሪካ ውድቅ መሆኑን የተመለከቱ ዘገባዎች ተካተዋል።

  • May 8 · 27 min

    የዓርብ ሚያዝያ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት

    ቀዳሚውን የዓለም ዜና በሚከተለው የዜና መጽሔት -የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)የቅድመ ምርጫ ሂደቶች ላይ ጥሰቶች እንደነበሩ መግለጹ ፣በአማራ ክልል በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ ተፎካካሪ ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስሞታ፣ ስለ መገናኛ ብዙኃን ምኅዳር የመንግሥት፣ የባለሙያዎች እና አጥኚዎች ዕዉነት፣ -የነዋሪዎችን ህይወት ያቃወሰው የትራንስፖርት እጥረት በኢትዮጵያ፣ -የሞት ፍርድን የሚጠባበቁትን ጨምሮ ሰነድ አልባዎቹ ኢትዮጵያዉያን በሳዉዲ፣ የዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን ተኩስ አቁም ወዴት ያመራ ይኾን? በተሰኙ ርዕሶች ስር የተጠናቀሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ ሳምንታዊ የወጣቶች ዓለምም በሰዓቱ ይቀርባል።

  • May 7 · 25 min

    የሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት

    በዜና መጽሔት የደቡብ አፍሪቃው ዘመቻ ዱዱላ’ ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ ሕገ-ወጥ ስደተኞችን እያደነ ነው፤ የወለንጪቲ የልማት ተነሺ ገበሬዎች ካሳ አልተከፈለንም ሲሉ ማማረራቸውን፤ የሙዝ አምራች አርሶ አደሮች የገበያ ተግዳሮት ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው ርዳታ እንዳይቋረጥ መጠየቁ እንዲሆም ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች 10 ቢልዮን ዶላር ለማግኘት ማቀዷ በሚሉ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ።

  • May 6 · 22 min

    የሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት

    አሜሪካ የኤርትራን ማዕቀብ ለማንሳት ማጤኗ ለኢትዮጵያ በረከት ወይስ መዘዝ? ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ኢትዮጵያውያን በተለየ መንገድ የጥቃት ኢላማ መሆናቸው የአላማጣና አካባቢው ወጣቶች የጦርነት ሥጋትና ስደት የሱዳን ክስና እና የኢትዮጵያ ምላሽ ህወሓት ትናንት የወሰደው 'ርምጃ እና የሚኖረው ውጤት

  • May 5 · 18 min

    የማክሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት

    ዛሬ ታስቦ የዋለዉን 85ኛ የኢትዮጵያዉያን የድል በዓል መታስብያን በማስታከክ ፤ የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም ሲል የሚያጠይቅ ዘገባን ይዘናል። ለ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ቅስቀሳ ተግዳሮት ገጠመን ያሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በደቡብ ወሎ ዞን እንዲሁም በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ላይ የተደረገው የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ እና የሚያሳድረዉ ጫናን የሚዳስስ ዘገቦችም በተከታታይ ይቀርባሉ። የአሜሪካዉ ትራምፕ በጀርመን ከሰፈሩ የአሜሪካን ወታደሮች መካከል ወደ 5,000 የሚሆኑትን ለማስወጣት እቅድ መያዛቸዉ እና የተሰጡ ግብረ መልሶችን የሚዳስስ ዘገባንም ይዘናል።

  • May 1 · 23 min

    የሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት

    የደቡብ አፍሪቃው መጤ ጠል እንቅስቃሴ ኢትዮጵያውያንን ብርቱ ስጋት ላይ ጥሏል አውሮፓ ሕብረት የፕሪቶሪያን ስምምነት አደጋ ላይ የሚጥሉ 'ርምጃዎች እንዲረግቡ ጠየቀ “አገልግሎታችንን ወደ አምስት ኮከብ ማሳደግ እንፈልጋለን” የኢትዮጵያ አየርመንገድ ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን በኢትዮጵያ ሲታወስ ወደ ከተሞች የሚደረግ ከፍተኛ ፍልሰት የቤት አቅርቦት ቀውስ ፈጥሯል-ተመድ

  • April 29 · 20 min

    የሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት

    ለኦሮሚያ ክልል ዘላቂ ሰላም መፍትሄ የሚሻው የወጣቶች ምክክር ፣ በአማራ ክልል የነዳጅ እጥረት ያስከተለው የኑሮ ምስቅልቅል ፣ ኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር የጀመረው የብትን ጭነት አገልግሎት ለኢትዮጵያ ይዞ የመጣው ዕድል ፣ «በኢትዮጵያ አካታች ዕርቅ ይምጣ» የኢትዮጵያውያን ሕዝባዊ ማኅበራት ጉባዔ በአሜሪካ፣ እንዲሁም አፍሪቃ ወደ ኋላ የቀረችበት የተመድ የምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች የትኞቹ ናቸው

  • April 28 · 20 min

    የሚያዝያ 20 ቀን 2018 የዜና መፅሔት

    በዜና መጽኄት አምስት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ።የኢትዮጵዊያን ግድያ በጆሃንስበርግ ፤ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ምርጫ ፤ ቁልፍ መሠረተ ልማቶችን ለመጠበቅ የተረቀቀው የሳይበር ደህንነት አዋጅ ምን ይዟል? እንዲሁም የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ወቅታዊ መግለጫ ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ።

  • April 27 · 18 min

    የሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት

    በዜና መጽሔት፤ የመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅ መብት እንዳይገድብ መጠየቁ ፤ ምርጫ ቦርድ የጸጥታ ሁኔታዎችን የሚያጣራ ቡድን ማሰማራቱ፤ ከፀሐይ ኃይል የሚያመነጭ ቴክኒዎሎጂ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ እንዲሁም የአፍሪካ የፖሊሲ አውጭዎች ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ትኩረት እንዲሰጡ የዘርፉ ባለሙያ ማሳሰባቸውን የሚያስቃኙ ዘገባዎች አካቷል።

  • April 24 · 26 min

    የሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሔት

    በዜና መጽሔት፤ በአርሲ ዞን ሮቤ ዲዳዓ ወረዳ ንጹሐን ላይ የተፈጸመው ጥቃት፤የአፍሪካ ሃገራት በሰብዓዊ መብት ላይ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን እንደማይተገብሩ ተገለፀ በ614 ምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ እንደሚያካሂድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጹ፤ ተዛብተው ተጽፈዋል የተባሉ ታሪኮች እንዲታረሙ ያሳሰበው የኦሮሞ ምርምር ማሕበር ጉባኤ ፤እንዲሁም እስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለሦስት ሳምንት መራዘሙን የሚያስቃኙ ዘገባዎች አካቷል።

  • April 23 · 23 min

    የሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት

    የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው እና አወዛጋቢ በሆኑት የምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች የመብት ጥሰት እየተፈፀመ ነው ሲል ሂውማን ራይትስ ወች መግለፁን ኢትዮጵያ ከነዳጅ ወደ ኤለክትሪክ መኪኖች ሽግግር እያደረገች መሆኑን፤ በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የኤለክትሪክ መኪና አጠቃቀም፣ እና መቋጫ ባጣው የአሜሪካ እና የኢራን ውዝግብ እንዲሁም የተዘጋው ሆርሙዝ ወሽመጥ

  • April 22 · 18 min

    የሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ዜና መፅሄት

    የዜና መጽሔታችን በአበርገሌ ወረዳ ስለተከሰተው ግጭት፤ የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመወዳደር ያቀረበውን ጥያቄ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሳይቀበለው መቅረቱ፤ የአውሮፓ ኮሚሽን ለአፍሪካ አገራት የበሽታ መከላከልና መቆጣጠሪያ ፕሮጀክት የሚውል ዕርዳታ መስጠቱ፤ እንዲሁም የአውሮፓ ኮሚሽን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ያስተላለፉት ውሳኔና አንደምታ በተመለከተ ከብራስልሱ ወኪላችን ያደረግነው አጭር ቆይታ ይዳሰሳሉ።

  • April 21 · 20 min

    የሚያዚያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሄት

    b,ዛሬ የዜና መጽሔታችን ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሰፊ ሥልጣን የሰጠው "የአቪዬሽን ደኅንነት" ማሻሻያ አዋጅ መፅደቅ፣ የነዳጅ እጥረት እና የትራንስፖርት ዋጋ መጨመር በአሶሳ ፣’"ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት እየተጣለብን ነው" ሲሉ የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች መግለፃቸው ፣እንዲሁም ቀነ ገደቡ እየተጠናቀቀ ያለው የተኩስ አቁም እና ተጠባቂው የኢስላማባድ ድርድር በተሰኙ ዘገባዎችን አካቷል። በቅደም ተከተል ይተነተናሉ።

  • April 20 · 15 min

    DW Amharic የሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዜና መጽሔት

    ህወሓት ከ2013 ዓ.ም በፊት የነበረው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ወደ ሥራ እንዲመለስ ወሰነ፣ ሕገወጥነትን ሕግ እንዴት ይቆጣጠረው? ጋዜጠኛ ሚሊዮን በየነ «አሁንም ያለበት ቦታ አይታወቅም» - አዲስ ስታንዳርድ

  • April 17 · 20 min

    የሚያዝያ 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት

    በዓለም ዜና የሚጀምረዉ የአንድ ሰዓቱ ስርጭታችን፤ በዜና መጽሔት ጥንቅሩ፤ 1, የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ እና መልስ የማግኛዉ መንገድ 2, በአማራ ክልል መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀያችን እንመለስ ጥሪ 3, ሕገ ወጥነትን ሕግ እንዴት ይቆጣጠረው? 4, በግጭት አፈታት እና በሰላም ግንባታ ላይ የተካሄደ ጉባኤ እንዲሁም 5, ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊነት የሚወዳደር የጋራ ዕጩ ያላፀደቀችዉ አፍሪቃ የተሰኙ ርዕሶችን አካቷል።

  • April 16 · 28 min

    የዜና መጽሔት፤ ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ሐሙስ

    በአማራ ክልል ራያ ቆቦ ወረዳ በጸበል ቦታ በደረሰ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ 8 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአደጋው ከ30 በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም። የአዲስ ስታንዳርድ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ማኔጂንግ ኤዲተር ትላንት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከሥራ ገበታው ከተወሰደ በኋላ ዛሬም የደረሰበት አልታወቀም። ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ሁለት የፖሊስ መኮንኖች እና አንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በታጣቂዎች ተገድለዋል። በዛሬው ዜና መጽሔት ከሚቀርቡ ዘገባዎች መካከል እነዚህ ይገኙበታል።