Skip to content
Artwork for Drum of Changes
Society & CultureGovernmentNewsPolitics

Drum of Changes

Zelalem Demissie

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard. But today, the call is unmistakable: Africa demands its rightful place at the table of global power.

Welcome to 'Drum of Changes' — a program dedicated to the stories that matter to Africa. Here, we explore culture, history, art, politics, the economy, and more, all through the lens of Africa itself. 'Drum of Changes' brings you the voices of transformation resonating across the continent.
Play
  • 53 episodes
  • Avg 59 min
  • English
Counted on this page — what you have heard stays on this device, so it is not something the list can be paged by.
  • S1 · E78
    Today · 1 hr

    ሩሲያ እና አፍሪካ፡ ነገን በአንድነት መገንባት

    ‍ ሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 28-29 ቀን፣ 2026 በሞስኮ ይካሄዳል። ጉባኤው በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ኃይል፣ የምግብ ዋስትና፣ ቴክኖሎጂ፣ ሎጂስቲክስ፣ ትምህርትና ጤና ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። “ሩሲያና አፍሪካ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እና የራስን የልማት መስመር የመከተል መብትን ለማስከበር የጋራ ቁርጠኝነት አላቸው፤ ይህም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በባህል ዘርፎች ዘላቂና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ትብብር ለመገንባት ሰፊ ዕድል ይፈጥራል” ሲሉ ዘላልም ተፈራ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም የኢትዮጵያ ታሪክና ማህበረሰቦች ጥናት ማዕከል ኃላፊ የሆኑትን ዘላለም ተፈራ (ዶ/ር) እንግዳ ባደረግንበት በዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ ሦስተኛውን የሩሲ-አፍሪካ ጉባኤ መነሻ በማድረግ በሩሲያና አፍሪካ ግንኙነት ውስጥ ያሉትን ዕድሎችና አቅጣጫዎች እንቃኛለን። እድገትን፣ ክብርንና ፍትሐዊ የዓለም ድርሻን ለምትፈልገው አፍሪካ ይህ አዲስ ምዕራፍ ምን ይዞ ይመጣል የሚለውንም እንመረምራለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E77
    Yesterday · 1 hr

    የአፍሪካ ድምፅ በባለብዙ ዋልታ የዓለም አቀፍ ሥረዓት ውስጥ

    የአፍሪካ ሀገራት ጠለቅ ያለ ጥያቄ በማንሳት ላይ ይገኛሉ፤ ጥያቄውም በዓለም አቀፍ መድረኮች መቀመጫ የማግኘት ብቻ ሳይሆን ደንቦቹን አብሮ የመጻፍም ጭምር ነው። በእርግጥ አፍሪካ ስለ አፍሪካ ከሚያወራ ይልቅ የሚያደምጣትና አብሯት የሚሰራ አዲስ የዓለም አቀፍ አሰራር መገንባት ትችላለች? በዛሬው የ ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በዲላ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ፖለቲካ ሳይንስ መምህር እና ተመራማሪ ከሆኑት ዳዊት መዝገበ (ዶ/ር) ጋር የምንወያየው በዚህ ጉዳይ ላይ ይሆናል።

  • S1 · E76
    Yesterday · 1 hr

    አንድ ድምፅ፦ አፍሪካ፣ ካሪቢያን እና የዓለም አቀፍ ፍትህ ትግል

    አፍሪካና ካሪቢያን የባርነትና ቅኝ ግዛት ታሪካቸውን ወደ የጋራ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ኃይል መለወጥ ይችላሉ? በዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ በኢትዮጵያ ለ15 ዓመታት ከኖሩትና በፓን-አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴዎች ላይ ከሚተጉት ጸሐፊና ተሟጋች ጃኔል ሆይሌት ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ እንወያያለን።

  • S1 · E75
    Friday · 1 hr

    የአፍሪካ ሀገር በቀል እውቀቶች እና የአዕምሯዊ ሉዓላዊነት

    አፍሪካ የሰው ልጅ መነሻ እንደመሆኗ የትምህርት ሥርዓቷን ከቅኝ ግዛት እሳቤ ተፅዕኖ ነፃ በማውጣት ሀገር በቀል እውቀትን የችግር መፍቻ ማድረግ ይገባታል። "የሰው ልጅ መነሻ የሆነችው አፍሪካ የራሷን ጥበብና ፍልስፍና በሥርዓቱ መጠቀም እንዳትችል የውጭ ጫና ተፅዕኖ አሳድሮባታል […] ከንግዲህ ግን ከውጭ በተወረሱ እሳቤዎች ላይ ብቻ ጥገኛ ሆኖ መቀጠል የሚቻልበት ሁኔታ እያበቃ ይመስላል [...] ከዚህ በኋላ አፍሪካ የራሷን ችግር በራሷ መፍታት ይኖርባታል" ሲሉ ታሪክ እና የሀገር በቀል እውቀቶች ተመራማሪ አህመድ ዘካሪያ (ፕ/ር) አህመድ ዘካሪያ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ የአፍሪካ ፍልስፍናዎች፣ የአስተዳደር ሥርዓቶች እና ሩሲያ ዙሪያ እናተኩራለን። ሀገር በቀል ዕውቀት ለአፍሪካ አስተዳደር መሠረት የሚሆንበትን እና የአስተሳሰብ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥበትን መንገድ ከታሪክ እና የሀገር በቀል እውቀቶች ተመራማሪ አህመድ ዘካሪያ (ፕ/ር) እና በጅማ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የኡቡንቱ የሕይወት ክህሎት ስልጠና ማዕከል መሥራች እውነቱ ኃይሉ (ዶ/ር) ጋር በመሆን እንቃኛለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በአማርኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E74
    Friday · 1 hr

    የቤት ባለቤትነት መላ፦ የኢትዮጵያ ጎረቤቶች ስለ ተመጣጣኝ የከተማ መኖሪያ ቤቶች ምን ያስተምሩናል?

    አብዛኞቹ የአፍሪካ ከተሞች ፈጣን ዕድገት እያሳዩ ቢሆንም፣ ከሚገነቡት ቤቶች ውስጥ ከሰባ በመቶ በላይ የሚሆኑት መደበኛ ባልሆኑ እና በቂ መሠረተ ልማት በማይሟላላቸው ሰፈሮች ውስጥ የሚገኙ ናቸው። “በሚቀጥሉት አሥርት ዓመታት ወደ አፍሪካ ከተሞች ለሚፈልሱ ከ600 እስከ 900 ሚሊዮን ወጣቶች አሁን ልማታዊ ትኩረት ካልተሰጠ ጉዳቱ ከባድ ነው። መሬት ለቤት ግንባታ ውድ ግብዓት በመሆኑም የመንግሥት መሬትን በመጠቀም፣ የመሬት ማስተካከያዎችን በማድረግ እና ከግል ባለቤቶች ጋር በመተባበር የተቀናጀ ልማት እውን ማድረግ ይገባል” ሲሉ ዩኤን-ሃቢታት) ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባች ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ። በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ የአፍሪካ ከተሞች ዕጣ ፈንታ በፈተናና በዕድል መካከል ባለበት በዚህ ወቅት የኑሮ ውድነትና የአየር ንብረት ጽናት ውይይቶችን እንቃኛለን። አፍሪካ የሌሎችን ጎዳና ከመከተል ይልቅ የራሷን የከተማ ልማት ጎዳና መቅረጽ ትችላለች ወይ? ለእነዚህ ጥያቄዎች ጥልቅ ምላሽ ለማግኘት ከተባበሩት መንግስታት የሰፈራ መርሃ ግብር (ዩኤን-ሃቢታት) ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባች ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉ። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E73
    October 8 · 1 hr

    ትርጉም እና አፍሪካ፡ በቋንቋዎች መካከል ድልድይ መዘርጋት

    አፍሪካ በሺዎች የሚቆጠሩ ቋንቋዎች መገኛ ስትሆን፤ ይህ የቋንቋ ብዝሃነት ለቀጣናዊ ውህደት እንደ ሀብት ሆኖ ያገለግላል። "ጥሩ ትርጉም ቃላትን ብቻ ሳይሆን ትርጉምን፣ እሴቶችን፣ ታሪክንና ባህልን ያስተላልፋል። ለአፍሪካ ትርጉም የብዙሃን ቋንቋ ተናጋሪነት ምሰሶ ነው፤ የባህልና የቋንቋ ልዩነቶች እንዳይጋጩ በማድረግ ማህበረሰቦች ሀገር በቀል ቋንቋቸውን እያዳበሩ በሰፊው የውይይት መድረክ ላይ እንዲሳተፉ ያስችላል" ሲሉ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ቋንቋዎችና ስነ-ጽሑፍ መምህር አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ የሙያዊ የትርጉም አገልግሎት የአፍሪካን ውህደት፣ ትምህርት፣ የሚዲያ ነፃነት እና የደቡብ ለ ደቡብ ትብብር ማጠናከር የሚችልባቸውን መንገዶች እንቃኛለን። በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ቋንቋዎችና ስነ-ጽሑፍ መምህር እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስና ሁማኒቲስ ኮሌጅ ዲን ከሆኑት አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ አድርገናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E72
    October 6 · 1 hr

    የሰላም መሰረቶች፡ በአፍሪካ አስተዳደር ሀገርበቀል ፍልስፍናን መጠቀም

    በሩዋንዳ የጋቻቻ ፍርድ ቤቶች የህብረተሰቡን ተሳትፎና የማካካሻ ልምዶች በመጠቀም፣ ከተለመዱት የፍትህ አካላት አቅም በላይ የሆኑ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ የዘር ማጥፋት መዝገቦችን በአስር ዓመት ውስጥ በብቃት መርምረዋል። “የራሳችንን ሀገርበቀል እሳቤዎች በሙሉ በአንድ ላይ አዋቅረን ብንይዝ፣ ለሌሎችም የሚተርፍ ትልቅ እሴት እና አሰራር አለን [...] ምናልባትም አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚስተዋሉትን ቅራኔዎች ሊፈቱ እና ሊያሻግሩን የሚችሉት እነዚህ እውቀቶች ናቸው” ይላሉ የጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና የአፍሪካ ጥናቶች ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ። በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ ከአፍሪካ ውጭ የተኮረጁ የአስተዳደር ሞዴሎች ያጋጠሟቸውን መዋቅራዊ ፈተናዎች ከጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲው ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ጋር በጥልቀት እንቃኛለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  • S1 · E69
    October 6 · 1 hr

    ዓባይ፣ ቀይ ባህር እና አፍሪካዊ ውይይት ፍለጋ

    '' ቀጣናዊ የማግለል ሙከራዎች'' ቢኖሩም የዓባይ 85 በመቶ ውሃ ምንጭነቷ እና ከቀይ ባህር ጋር ያላት ታሪካዊ ቅርበት ያለ ኢትዮጵያ ንቁ ተሳትፎ በምሥራቅ አፍሪካ የሚደረግ ማንኛውም ዘላቂ የጸጥታ ወይም የንግድ ውጥን እንዳይሳካ ያደርገዋል። “በቪየና የውል ሕግ ስምምነት አንቀጽ 34 መሠረት፣ የጋራ መግለጫው ያለ ሶስተኛ ወገን ግልጽ ፈቃድ በላዩ ላይ ግዴታዎችን መፍጠር አይችልም። ኢትዮጵያ በስብሰባው ላይ ያልተሳተፈች እና ያልፈረመች በመሆኗ፣ ጽሑፉ በኢትዮጵያ የውሃ አስተዳደር እና በህዳሴው ግድብ አሠራር ላይ ምንም ዓይነት ሕጋዊ የበላይነት የለውም” ሲሉ ከኢኮኖሚ ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ። የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ የኤል አላሜይን የጋራ መግለጫ በዓባይ ወንዝ አስተዳደርና በቀይ ባህር ጸጥታ ላይ ይሚኖረዉን ጂኦፖለቲካዊ ፋይዳ ይዳስሳል። እንዲሁም የኢትዮጵያን ስልታዊ ምላሽና እውነተኛ የፓን-አፍሪካ ውይይት አስፈላጊነትን የመለከታል። ለዚህም ከኢኮኖሚ ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E68
    October 5 · 1 hr

    ስለአዲሱ የዓለም ሥርዓት ከቫልዳይ የተሰማው መልዕክት

    ፕሬዚዳንት ፑቲን ዓለም ወሳኝ የእጥፋት ነጥብ ላይ መድረሷን ገልጸው፤ ዓለማችን ሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ደህንነትንና የዓለም አቀፍ ኃይልን ሊቀርጽ የሚችልበት አዲስ የቴክኖሎጂ ዘመን ላይ መሆኗን አፅንኦት ሰጥተዋል። “ምዕራባውያን ሌላ ጠንካራ አገር እንዲፈጠር አይፈልጉም፤ ቢፈጠርም በተለያየ መልኩ ያዳክሙታል። ሩሲያ ከናቶ እና ከምዕራቡ ዓለም ጋር በዩክሬን የገጠማት ጦርነት አንዱ ማሳያ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ አፍሪካም በኢኮኖሚና በሌሎች ዘርፎች ራሴን ልቻል የሚለ ሀገር ብቅ ቢል በተለያዩ መንገዶች ለማዳከም የሞክራሉ” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ድሀንነት ተቋም መምህርና ተመራማሪ ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን በቫልዳይ የውይይት ክለብ 2026 የመዝጊያ ስነ-ሰርዓት ላይ ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር፣ ከባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት እና ለአፍሪካ ከሚኖረው ፋይዳ አንፃር የምንቃኝበት ነው። ለዚህም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላም እና ደህንነት ተቋም መምህር እና ተመራማሪ ከሆኑት ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር) ጋር አውርተናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  • S1 · E67
    October 3 · 1 hr

    ስለአዲሱ የዓለም ሥርዓት ከቫልዳይ የተሰማው መልዕክት

    የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን በቫልዳይ የውይይት ክለብ 2026 የመዝጊያ ስነ-ሰርዓት ላይ ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር፣ ከባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት እና ለአፍሪካ ከሚኖረው ፋይዳ አንፃር የምንቃኝበት ነው። ለዚህም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላም እና ደህንነት ተቋም መምህር እና ተመራማሪ ከሆኑት ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር) ጋር አውርተናል።

  • S1 · E66
    October 3 · 1 hr

    የአፍሪካ የሰላም ጎዳና፦ በባህላዊ ተቋማት የሚደረግ ግጭት መከላከል

    በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ አፍሪካ በአገርበቀል ተቋሞቿ አማካኝነት ግጭትን ለመከላከልና ሰላምን ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት ይዳስሳል። ለዚህም ከደኅንነት ጥናት ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ከሆኑት ከሙሳ ሱማሆሮ ጋር ቆይታ አድርገናል::

  • S1 · E65
    September 30 · 1 hr

    አፍሪካ እና ጊዜ፣ በማን ሰዓት ላይ ነን?

    በአፍሪካ የእጅ ሰዓት ከመግባቱ ከብዙ ዘመናት በፊት፣ ጊዜ የሚለካው በሜካኒካል ሰዓት ቁጥሮች ሳይሆን የተፈጥሮ ዑደቶችን በጠበቁ ክስተቶች ነበር። “የአፍሪካ የጊዜ አቆጣጠር ከምዕራባውያን የጊዜ ጽንሰ-ሐሳብ ፈጽሞ የተለየ ነው። ይኸውም ጊዜ በማህበራዊና ባህላዊ መነጽር የሚታይ፣ መኖርና ሊለማመዱት የሚገባ ክስተት በመሆኑ፣ ባለፈውና በአሁኑ ጊዜ ውስጥ ባሳለፍናቸው ነገሮች ላይ ትርጉም ሰጥተን እንድንገነዘበው ያስችለናል” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካና እስያ ጥናቶች ማዕከል መስራች አባል ጌታቸው ካሳ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የአፍሪካን የጊዜ ጽንሰ-ሐሳብ ከዘመናዊው አለም ጋር ያለው ግንኙነት በመዳሰስ በባህላዊ እና በሰዓት ላይ በተመሰረቱ ስርአቶች መካከል ያለውን ልዩነት እንቃኛለን። ማህበራዊ አንትሮፖሎጂስት እና የአፍሪካ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካና እስያ ጥናቶች ማዕከል መስራች አባል ጌታቸው ካሳ (ዶ/ር) በዛሬው ርዕሳችን ዙሪያ ሐሳባቸውን አጋርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E69
    September 29 · 1 hr

    ከድምፅ እስከ ታሪክ፡ የግሎባል ደቡብ ሕዝቦችን የሚያስተሳስረው የቋንቋ ገመድ

    ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ አማርኛን ማስተማር ከጀመረ 14 ዓመታት ማስቆጠሩ፣ በቻይና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የኢትዮጵያን ባህልና ቋንቋ በቀጥታ ለማስተዋወቅ ትልቅ ድልድይ ፈጥሯል። “ይህማ [ቋንቋ] በጣም ትልቅና የላቀ ሚና አለው። ቋንቋ በሁለት ሕዝቦችና በሁለት አገሮች መካከል እንደ ድልድይ የሚያገለግል ቁልፍ ጉዳይ ነው። ቻይናውያን አማርኛን ሲማሩም በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የንግድ፣ የልማትና የዲፕሎማሲ ሥራዎችን በቀጥታ ለመረዳት ያስችላቸዋል” ሲሉ በቻይና የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ መምህርትና አስተባባሪ ስንቅነሽ አጣለ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት ቋንቋ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክርበትን መንገድ ይዳስሳል። እንግዳችን በቻይና የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ መምህርትና አስተባባሪ ስንቅነሽ አጣለ (ዶ/ር) ናቸው። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  • S1 · E68
    September 29 · 1 hr

    ከአፍሪካ ወሰን ባሻገር፡ የስደት ፖሊሲዎችን ማን፣ ለምን ይቀርጻል?

    የአውሮፓ ሀገራት የስደት እና የድንበር ፖሊሲ ድንበራቸውን በራሳቸው አካባቢ ብቻ የሚገድብ ሳይሆን፣ ስደትን ከመነሻው እና ከመሸጋገሪያ ሀገራት ጀምሮ ሄዶ መቆጣጠር ላይ ያተኮረ ነው። “አውሮፓ ሀገራት የውጪ ድንበራቸውን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት የስደት ቁጥጥር ፖሊሲያቸው በአፍሪካ መነሻ እና መሸጋገሪያ ሀገራት ውስጥ ዘልቆ በመግባት ስደትን ከምንጩ ለመቆጣጠር ላይ ያተኮረ ነው [...] አውሮፓውያን በስደት ቁጥጥር ሰበብም የአፍሪካውያን ፖሊሲዎች [የፍልሰት] ቀረፃ ሂደት ላይ ጫና ያሳድራሉ” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብአዊ መብቶች ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር ሜሮን ዘለቅ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት፤ በአፍሪካ እና በአውሮፓ መካከል ስላለው የስደት አስተዳደር፣ አህጉራዊ አቅጣጫዎች፣ የሉዓላዊነት ተግዳሮቶች፣ እንዲሁም የሰለጠነ ሰውኃይል ፍልሰት ላይ ሰፊ ዳሰሳ እናደርጋለን። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብአዊ መብቶች ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ሜሮን ዘለቀ (ዶ/ር) ደግሞ እንግዳችን ናቸው። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በአማርኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E67
    September 29 · 1 hr

    የብሪክስ ንግድ፦ አዳዲስ ዕድሎች፣ አዳዲስ ገበያዎች

    የብሪክስ አባል አገራት እርስ በርሳቸው የሚያደርጉት የንግድ ልውውጥ መጠን ከሃያ ዓመታት በፊት ከነበረበት 84.2 ቢሊዮን ዶላር በብዙ እጥፍ አድጎ 1.17 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ደርሷል። “የብሪክስ ኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ የዶላር ጥገኝነትን በመቀነስ ዓለምን ወደ ባለብዙ ዋልታ ኢኮኖሚ እያሸጋገረ ነው [...] ኢትዮጵያም አባል መሆኗ [የብሪክስ] የንግድ ማዕቀፎችን ለማብዛት፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና ቴክኖሎጂ ለማግኘት ትልቅ ዕድል ይፈጥርላታል” ሲሉ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ማኔጅመንት የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ ዱጋሳ ሙሉጌታ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ጉባኤ የ2026 የብሪክስ ንግድ ዘገባ ላይ ዳሰሳ በማድረግ፣ የብሪክስ መስፋፋት ለኢትዮጵያ የወጪ ንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት የሚፈጥራቸውን ዕድሎች በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ማኔጅመንት የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ ዱጋሳ ሙሉጌታ (ዶ/ር) ጋር ይቃኛል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  • S1 · E66
    September 29 · 1 hr

    የነጻነት ዋጋ – የሃይቲ ያልታየው ገፅ

    የመጀመሪያዋ ነፃ የጥቁር ሪፐብሊክ የሆነችው ሃይቲ ዛሬ ላለችበት ውጥንቅጥ ምክንያት የጥቁር ህዝብ ድክመት ሳይሆን፣ የሁለት ክፍለ ዘመናት የምዕራባውያን የሀብት ዘረፋ እና የጣልቃ ገብነት ሴራ ውጤት ነው። “የሄይቲ ወቅታዊ ችግሮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከሀገሪቱ የመጀመሪያ ስቴት ምስረታ ጀምሮ የጀመሩ ናቸው፤ አሜሪካውያንም ሄይቲን የጥቁር ነፃነት ፊት አውራሪ በመሆኗ እና ይህ አስተሳሰብ ወደ ሰሜን አሜሪካ ሊዛመት ይችላል በሚል ስጋት ይመለከቷታል” ሲሉ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቱዩት የባለብዙ ወገን መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጉዳዮች ተመራማሪ አዲስ አለማሁ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ያልተነገረውን የሃይቲ የጀግንነት ታሪክ እና የምዕራባውያን ታሪካዊ በደሎች ሀገሪቱን ላለችበት ውጥንቅጥ እንዴት እንደዳረጓት በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቱዩት የባለብዙ ወገን መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጉዳዮች ተመራማሪ አዲስ አለማሁ ጋር ዳሰሳ አድርጓል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  • S1 · E64
    September 28 · 1 hr

    ሁለተኛው “የዓለም" ጦርነትና የተረሱት የአፍሪካ ተዋጊዎች

    በዛሬው የ ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት፤ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን በቅኝ ግዛት ሠራዊት ተመልምለው የጦርነቱን ውጤት መቀየራቸውን እና ጦርነቱ ሲያበቃ ወደ አድሎአዊ ጡረታና ቀጣይ የቅኝ አገዛዝ መመለሳቸውን እንቃኛለን። እንግዳችንም በአሜሪካ ኮርኔልና በመቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ታሪክ ያስተማሩትና አሁን በኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ መምህር የሆኑት አየለ በከሪ (ዶ/ር) ናቸው።

  • S1 · E63
    September 28 · 1 hr

    የመስቀል በዓል መንፈሳዊ ፋይዳ፣ ታሪካዊ አመጣጥ እና የትውልድ ኃላፊነት

    የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ትኩረት ያደረገው የመስቀል በዓል በመንፈሳዊና ታሪካዊ አመጣጡ፣ በዓለም አቀፋዊ ማህበራዊ ትስስሩ እንዲሁም አዲሱ ትውልድ ይህንን የዘመናት እሴት እንዴት ይዞ መዝለቅ እንዳበት ላይ ነው። ለዛሬው ውይይታችን እንግዳችን የሆኑት የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን መምህር ቀሲስ አንድነት አሸናፊ ናቸው።

  • S1 · E62
    September 28 · 1 hr

    ምስራቃዊው እጥፋት፡ ራሽያ፣ ቻይና እና አዲሱ መካከለኛው ምስራቅ

    በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት ሩሲያና ቻይና የምዕራባውያንን የበላይነት በመገዳደር ለአሜሪካ ጣልቃ ገብነት አማራጭ ማቅረባቸውን እና የአዲስ ምዕራፍ መሠረት መሆናቸውን እንቃኛለን። በጉዳዩ ላይ ከቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ አማካሪ እና የአፍሪካ ሕብረት ፀረ-ሙስና ቦርድ ሊቀመንበር ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋ (ዶ/ር) ጋር አውርተናል።

  • S1 · E61
    September 28 · 1 hr

    ቋንቋዎች በአህጉራት መካከል እንደተዘረጋ ድልድይ

    የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት ቋንቋ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክርበትን መንገድ ይዳስሳል። እንግዳችን በቻይና የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ መምህርትና አስተባባሪ ስንቅነሽ አጣለ (ዶ/ር) ናቸው።

Showing 1–20 of 53 episodes