
Drum of Changes · August 6 · 1 hr
የኤደን ባሕረ ሰላጤ፡ የባሕር ወንበዴዎች እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂክ አስፈላጊነት
0:00-1:00:04
transcript
show notes
የዓለም አቀፉ የባህር ላይ ጉዞ ድርጅት በሶማሊያ የባህር ዳርቻ እና በኤደን ሰላጤ ላይ የባህር ላይ ወንበዴዎች ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ "አሳሳቢ ነው" ብሏል።
“ሩሲያ ትራዲሽናል (ባህላዊ) የኢትዮጵያ አጋር ነች ስንል መንግስታት ቢቀያየሩ እንኳን የማይቀያየር ወዳጅነት ነው ያላቸው ማለት ነው። የአድዋን ጦርነት ብናነሳ እንኳን [ከኢትዮጵያ ጋር የቆመች] ብቸኛዋ የአውሮፓ ሀገር ነች አይደለም? [...] ለአፍሪካውያንም እኮ ከሩሲያ የሚቅድም ወዳጅ የለም [...] ዛሬ ሩሲያ የባለብዙ ዋልታ ዓለም ስረዐት ወሳኝ አካል መሆኗ ወደአንድ ወገን አዘንብሎ የነበረውን የአዓለም ግንኙነት ስረዓት ሚዛን ለማስጠበቅ አስችሏል” ሲሉ የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ እንዳለ ንጉሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የዛሬው ድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ያላትን የጠበቀ ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሠረት በማድረግ በኤደን ሰላጤ ላይ የባህር ላይ ውንብድናን ለመከላከል ልትጫወት የምትችለውን ስልታዊ ሚና እንቃኛለን። ለዚህም በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር እንደለ ንጉሴ እንግዳችን ናቸው።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ: