
የተዘረፉ ቅርሶች፡ የአፍሪካን የታሪክ እውነት ለማስመለስ የሚደረገው ዓለም አቀፍ ትግል
transcript
show notes
“[…] ከአፍሪካ በጉልበት የተወሰዱ የተለያዩ ቅርሶች ለአፍሪካውያን ባለቤቶቻቸው ሳይመለሱ በአውሮፓ ሙዚየሞች እንዲቆዩ የሚደረገው ደህንነታቸው በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠበቅ ነው የሚለው መከራከሪያ እውነታነት የለውም። ምክንያቱም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአውሮፓ ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሙዚየሞች በጦር መሳሪያውች ተደብድበዋልና። በቅርቡ በፈረንሳዩ ሉቭር ሙዚየም ጭምር በርካታ ስርቆቶች ተፈጽመዋል። ስለዚህ በምዕራቡ አገራት ያሉ ሙዚየሞች በሙሉ አስተማማኝ ናቸው ማለት አይቻልም” ሲሉ የማህበራዊ ጉዳዮች ተመራማሪው አሉላ ፓንከረስት (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚ ጉዳዩ፣ የአፍሪካን የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ትክክለኛ መኖሪያቸው ለመመለስ የሚደረገውን ታሪካዊ፣ ስልታዊ እና ጥልቅ ስሜት የሚንጸባረቅበትን አፍሪካዊ እንቅስቃሴ ያስቃኘናል። ለዚህም የማህበራዊ ጉዳዮች ተመራማሪውን አሉላ ፓንከረስት (ዶ/ር) አነጋግረናል። እ.ኤ.አ. ሰኔ 12 እና 12 ቀን 2026 በአዲስ አበባ የተካሄደው አንደኛው ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ እና የቴክኖሎጂ ውድድር ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የምንቃኝበት ሁለታኛው ጉዳያችን ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ደግሞ ሐሳባቸዉን ሊያጋሩን ብሩክ ከድር (ዶ/ር)፣ አናንድ አንባላጋን እና ፋራይ ቺዳሩን አነጋግረናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ: