
transcript
show notes
"ዓለም አቀፉ ደቡብ አሁን ከቡድን 7 በበለጠ የዓለምን ኢኮኖሚ በበላይነት እየተቆጣጠረ ነው [...] አዲስ የገንዘብ ሥርዓት ማለት፡ የዶላር ተፅዕኖን የመቀነስ ሂደትን ያፋጥናል፣ አሜሪካ ዶላር በእጇ በመሆ ምክንያት በሀገራት ላይ የምትጥለው ማዕቀብ ታሪክ ሆኖ እንዲቀር ያደርጋል” ሲሉ የኢኮኖሚ ባለሞያ እና የፖሊሲ አማካሪ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የምዕራቡ ዓለም ሀገራት ኢኮኖሚያዊ መሰናክሎችን በግንባር ቀደምትነት እየደረደሩ ባሉበት እና ነባር ባለብዙ ወገን ስምምነቶችን ስጋት ላይ በሚጥሉበት በዚህ ወቅት፣ ጠለቅ ያሉ ሁነቶችን መረዳት ለአፍሪካ ስትራቴጂካዊ የወደፊት ጉዞ የሚኖረውን ወሳኝነት እና ከዚህም አንፃር የታዳጊ ኢኮኖሚ ባለቤቶች የሚኖራቸውን የፖሊሲ አማራጮች በጥልቀት እንመረምራለን። ቆስጠንቲኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በከፍተኛ የፖሊሲ አማካሪነት ያገለገሉ፣ በአፍሪካ ህብረት የፀረ-ሙስና ቦርድ መሪነት የቆዩ ታዋቂ የኢኮኖሚ ባለሞያ እና የፖሊሲ አማካሪ ሲሆኑ፣ በቅርቡም “ታሪፍስ ኤንድ ‘ኒዉክሌር’ ትሬትስ ኦቭ ኤ ኒዉ ኮልድ ዎር” የተሰኘ አዲስ መጽሐፋቸው ልንባብ አብቅተዋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ: