
0:00-12:29
Streams straight from the publisher. podnod never proxies or re-hosts episode audio.
አርዕስተ ዜና
ሰባተኛው ዙር የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ መራጮች ዛሬ ለፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት ለሚወዳደሩ እጩዎች ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል። የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ክልል በበሻሻ ከተማ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ታዬ ዐፅቀ ሥላሴ ደግሞ በአዲስ አበባ ዛሬ ጠዋት ድምጽ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “በጸጥታ ምክንያት ወደ 143 የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ” አለመከፈታቸውን ዛሬ አስታወቀ። የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተ ወርቅ ኃይሉ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የተወሰኑ የምርጫ ክልሎች የድምጽ አሰጣጥ ከተጀመረ በኋላ በጸጥታ ችግር መቋረጡን ተናግረዋል።
No links were found in this episode’s notes.