Skip to content
Artwork for Drum of Changes
Society & CultureGovernmentNewsPolitics

Drum of Changes

Zelalem Demissie

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard. But today, the call is unmistakable: Africa demands its rightful place at the table of global power.

Welcome to 'Drum of Changes' — a program dedicated to the stories that matter to Africa. Here, we explore culture, history, art, politics, the economy, and more, all through the lens of Africa itself. 'Drum of Changes' brings you the voices of transformation resonating across the continent.
Play
  • 66 episodes
  • Avg 59 min
  • English
Counted on this page — what you have heard stays on this device, so it is not something the list can be paged by.
  • S1 · E30
    April 11 · 59 min

    ለዘላቂ ሰላም ወይስ ለዳግም ጦርነት ዝግጅት? የኢራን-አሜሪካና እስራኤል የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም እንቆቅልሽ

    “ኢራን እና አሜሪካ መሰረታዊ የግጭት መንሳኤ የሆኑ ጉዳዮችን በተመለከተ መግግባባት ላይ ከደረሱ ወደ ዘላቂ ሰላም ሊመጡ ይችላሉ። ነገር ግን እነዚህን መሰረታዊ መንሳኤዎች መፍታት ከልቻሉ፣ ይህ የሁለት ሳምንት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ጊዜ በመግዛት አቅም አሰባስበው ዳግም ወደጦርነት ለመመለስ የሚያስችላቸውን ሁኔታ እየፈጠሩ ሊሆን ይችላል" ሲሉ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት የመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ ተመራማሪ መሐመድ ሰኢድ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጉዳያችን በፈርጆቹ መጋቢት 8፣ 2026 ኢራን እና አሜሪካ የተስማሙበትን የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ስፋት ይቃኛል። በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት ከፍተኛ ተመራማሪ መሐመድ ሰኢድን (ዶ/ር) አነጋግረናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ በፈርጆቹ መጋቢት 7፣ 2026 በሆርሙዝ ሰርጥ የመጓጓ ነፃትን ለማስከበር የኃይል አማራጭን ለመውሰድ የጸጥታው ምክር ቤት ቀርቦ የነበረውን ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ በሩሲያና ቻይና ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ውድቅ መሆኑን እንመለከታለን። ይህ ሁኔታ አቅሙ እየተዳከመ ስለመጣው የምዕራቡ ዓለም ሁኔታ ምን ይነግረናል? የእዮብዘር ዘውዴ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር በዚህ ጉዳይ ዙሪያ አስተያየታቸውን አጋርተዉናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  • S1 · E29
    April 7 · 1 hr

    አፍሪካን የመበየን አባዜ፤ የምዕራባውያን የጥናት ተቋማት የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም መሣሪያነት

    “የምዕራባውያን ስረዓቶች በአመፃ የታጀቡ ናቸው። ዛሬ በዓለም ዙሪያ ያሉትን ብዙ ግጭቶች ብንመለከት፣ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የምዕራባውያን እጅ አለበት። ይህንን ሁኔታ በተመሳሳይ ቀውስ ውስጥ ሁለት ሚና ይዞ መገኘት እለዋለሁ። ችግር ፈጣሪዎች ለችግሩ ስም ያወጡለታል፣ ለፈጠሩት ችግር ደግሞ መፍትሄ ፈጣሪዎች ሆነው ይመጣሉ። ይህ ምዕራባውያን መገለጫ ነው” ሲሉ በደቡብ አፍሪካው ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ምርምር ባልደረባ ቺዶካሼ ንዬሬ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሩ። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ጉዳያችን አፍሪካ የምትታይበትን እይታ የሚቀርፀው ማነው ስንል እንተይቃለን። ለዚህም በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የታቦ ምቤኪ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች የድህረ ምረቃ ምርምር ባልደረባ ቺዶካሼ ንዬሬን (ዶ/ር) አነጋግረናል። ሁለተኛ ጉዳያችን ደግሞ 10ኛው የኢትዮ ጤና ኤግዚቢሽን እና ኮንግረስ 2026 ላይ የሚያተኩር ይሆናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E27
    April 1 · 1 hr

    የአውሮፓ አይሁዶችን በኢትዮጵያ ለማስፈር ተይዞ የነረው ውጥና የኢትዮጵያ ምላሽ

    “እርግጥ ነው፣ ሐሳቡ [የአውሮፓ አይሁዶችን በኢትዮጵያ ማስፈርን] በተመለከተ ለንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የተላከው ደብዳቤ እንግሊዝ እና አሜሪካ መንግሥት ድጋፍ ነበረው። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት በአንድ አገር ውስጥ ሌላ አገር ለመፍጠር የሚያስችል ይሁንታ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ምክኛቱም ይህንን መፍቀድ የአገሪቱን ሉዓላዊነት አሳልፎ የሚሰጥ ነውና” ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርኸተሰፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ጉዳያችን ወቅታዊውን የመካከልኛው ምስራቅ ሁኔታ መነሻ አድርገን በኢትዮጵያ የቀድሞው ሐረር ጠቅላይ ግዛት የአውሮጳ አይሁዶችን ለማስፈር ተይዞ የነበረው ውጥን እና የኢትዮጵያን ምላሽ ያስቃኘናል። በቀደመው ጊዜ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ቆስጠንጢኖስ በርኸተሰፋ (ዶ/ር) አነጋግረናቸዋል። የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ጤና ባለሙያ እና ምሁር እንዲሁም ተመራማሪ የሆኑትን ኃይሉ ታምሩን (ዶ/ር) አነጋግረን ሰው ሰራሽ አስተውሎ በአፍሪካ የጤና ምርምርን ከማገዝ አንፃር የሚኖረዉን ሚና ቃኝተናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E26
    March 30 · 1 hr

    የፈውስ ክር:- በሚገባው ልክ ያልታወቀው በገና

    በገና በመንፈሳዊ ዝማሬዎች ውስጥ ካለው ቦታ ባለፈ፣ ለመንፈሳዊ ፈውስነት መዋል የሚችል ጥንታዊ እና ጥልቅ ሚስጥር ያለው ማሳሪያ ነው። “ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ንዝረቶችን ያመነጫሉ ... ይህ ደግሞ የሰዎችን አዕምሮ ሎም አካል ሊጎዳ ይችላል። ይሁን እንጂ በገና በተቃራኒው ከዚህ በተለየ መልኩ ጥቅም ይሰጣል ... የውስጥ ሰላምን እና እርጋታን የሚያጎናፅፉ ንዝረቶችን ያመነጫል” ሲሉ ፕሮፌሰር ብረሃኑ ግዛው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ ጥንታዊ እና የጥልቅ መንፈሳዊ ዝማሬ ማጀቢያዎች መካከል በገና እንቃኛለን። በገና ለመንፈሳዊ ፈውስ መዋል ስለመቻሉም እናነሳለን። ለዚህም ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሓላፊ እና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ጠባቂ፣ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ግዛው የድምፅ ኢንጅነር፣ አቶ ካሳሁን ሓይለማሪያም የማሕበረቅዱሳን ሰብሳቢ፣ እንዲሁም ብሌን ዮሴፍ የሙዚቃ መምህርት እና ባለሞያን አነጋግረናል። ሙሉ መረጃ ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራምን ያዳምጡ:

  • S1 · E25
    March 26 · 1 hr

    የሕዝብ ቁጥር ፖሊሲ እንደ ጂኦፖለቲካ መሣሪያ፡- ‘የኪሲንጀር ሪፖርት’ እና የደቡቡ ዓለም እውነታ

    “የህዝብ ቁጥር መጨመርን በመግታት ላይ ብቻ አላተኮሩም [ምዕራባውያን]። በአዳጊ ሀገራት ውሰጥ የህዝብ ቁጥር መጨመርን በመግታት፣ የሀገራቱን ሀብት ለመበዝበዝ የሚያመች ስትራቴጂ እየከተሉ ነበር። ይህ ያፈጠጠ የብዝበዛ አካሄድ ነው። ምክንያቱም በእነዚህ ሀገራት አነስተኛ የህዝብ ቁጥር መኖር ማለት ለምዕራቡ ዓለም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ቁጥጥር ወይም ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ ቀላል ይሆንላቸዋል” ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን እ.ኤ.አ. በ1974 በአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ምክርቤት የተዘጋጀውንና ‘የኪሲንጀር ሪፖርት’ በመባል የሚታወቀውን ሰነድ በማዳሰስ ላለፉት አስርት ዓመታት የምዕራቡ ዓለም በተለይም በተመረጡ 13 የደቡቡ ዓለም ሀገራት ላይ ትኩረት በማድረግ፣ የህዝብ ቁትራቸው እንዳያድግ ሲከተለው የነበረውን ስትራቴጂ እንፈሻለን። በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ጋር ቆይታ በማድረግ ይህንን ሰነድ ፈትሸነዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E24
    March 24 · 1 hr

    ካሳ እና ፍትህ፡ በፓን አፍሪካዊ ማህደረ ትውስታ እና በዓለም አቀፍ የኃይል ፖለቲካ መካከል

    “አፍሪካ የራሷን ታሪክ፣ የራሷን እውነታ ለዓለም የምትነግርበት ድምፅ ይኖራት ዘንድ ፍፁም አስፈላጊ ነው። ምክኛቱ ደግሞ እስከዛሬ ድረስ አፍሪካን ብሎም የአፍሪካን ታሪክ በራሳቸው መንገድ ሲተርኩ ስለአፍሪካ ሲናገሩ የቆዩት አውሮፓውያን ናቸውና። ከአፍሪካ ውጭ [በአሜሪካ] እንዳደገች አንዲት ጥቁር ሰው እውነቱን ለመናገር ስለአፍሪካ መልካም ነገር ሰምቼ አላውቅም” ሲሉ ፓናፍሪካኒስቷ ጃኔል ሆይሌት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የባሪያ ንግድ፣ የቅኝ ግዛት እና መዋቅራዊ ብዝበዛ በጥቁር ሕዝቦች ላይ ጥሎ ስላለፈው አሻራ እንቃኛለን። ጨምረንም መላው የጥቁር ሕዝቦች ለፍትህ እና ካሳ የሚያደርጉትን የትግል ጉዞ እንመለከታለን። በዚህ ጉዞ ውስጥም ለጥቁር ሕዝቦች የቆሙ ተቋሟት ዛሬም ድረስ ከቀጠለው የቀድሞ ቅኝ ገዥዎች ግብዝነት ጋር የሚያደርጉትን ትግል እንፈትሻለን። ለዚህም ታዲያ ኑሯቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉት ጥቁር አሜሪካዊቷ ፓናፍሪካኒስት፣ ደራሲ እና ወደ አፍሪካ የመመለስ ንቅናቄ አንቂ ጃኔል ሆይሌትን ጋብዝን በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ ሐሳባቸውን አጋርተዉናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

Showing 61–66 of 66 episodes