
transcript
show notes
የአፍሪካ መሪዎች ለሦስተኛው የሩሲያና አፍሪካ ጉባኤ ሞስኮ የተሰበሰቡት ለስምምነት መፈራረም ብቻ አልነበረም፤ ይልቁንም አጋርነቱ ለወጣቶቻቸው ፋብሪካን፣ እርሻን፣ ትምህርትን፣ የኃይል ማመንጫዎችንና የሥራ ዕድልን ማምጣት ይችላሉ ወይ? የሚል ትልቅ ጥያቄ አንግበው ነበር። ባዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ታዲያ ሁለቱ አካላት ከዚህ ጉባኤ ምን አተረፉ ስንል በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር እና ተመራማሪ ከሆኑት እንግዳችን ዳዊት መዘገበ (ዶ/ር) ጋር በመሆን እንጠይቃለን።