
transcript
show notes
ኢትዮጵያና ሩሲያ ወደ 130 ዓመታት የተጠጋ የዲፕሎማሲ ታሪክ አላቸው። ዛሬ ደግሞ በብሪክስ እና በባለብዙ ኃይል ማዕከላት ዓለም አቀፍ ሥርዓት ውስጥ ያላቸው አጋርነት ለአፍሪካ ሉዓላዊነትና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ይገኛል።
“ሩሲያ ለአፍሪካ የቬቶ መብት በመጠቀም ጠበቃ ሆና መቆየቷ ትልቅ ሚና ቢኖረውም፣ አፍሪካውያን የራሳቸው ቋሚ ውክልና ኖሯቸው ድምፃቸውን በራሳቸው ማሰማት እንዲችሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ራሱን መፈተሽ እና ማደስ ይኖርበታል” ሲሉ ናኒ ደበሌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
3ኛውን የሩሲያ አፍሪካ ጉባዔ መነሻ በማድረግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማህብረሰብ ራዲዮ ኤፍ.ኤም 99.4 ጋር በመሆን በምናዝጋጀው የዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ልዩ ዝግጅታችን፣ ሦስተኛውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ እንቃኛለን። የሁለቱን ወገኖች ታሪካዊ ትስስር፣ የትብብር ዕድሎችና ተግዳሮቶች፣ እንዲሁም የአፍሪካና የኢትዮጵያን ጥቅም እንዴት እንደሚያስቀጥል እንመረምራለን። ለዚሁ ጉዳይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ናኒ ደበሌን እንግዳ አድርገናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ: