
transcript
show notes
በ15 የአፍሪካ ሀገራት በተደረገ ጥናት፣ ከዜናዎች አንድ ሶስተኛው ከውጭ ምንጮች የተገኙ ሲሆን፣ አራተኛውን ድርሻ ዋና ዋናዎቹ የምዕራባውያን የዜና ኤጀንሲዎች ይዘዋል። ከእነዚህ ዘገባዎች 81 በመቶ ያህሉ በችግሮች ላይ፣ 13 በመቶው ደግሞ በግጭትና በአመፅ ላይ ያተኮሩ ናቸው።
“ነባሩ የዓለም ሥርዓት ግሎባል ሳውዝ [የደቡቡ ዓለም] ጥሬ ዕቃ አቅርቦ የምዕራባውያኑን ጎተራ ከመሙላት ባለፈ፣ እሴት ጨምሮ እንዳያመርት መዋቅራዊ ጫና ያደርግበታል። መገናኛ ብዙሀን ደግሞ ይህንኑ ኢፍትሃዊ ትርክት ማስፈጸሚያ መሣሪያ ሆኖው ያገለግላሉ። በመሆኑም ይህንን አካሄድ አፍሪካ የራሷን የመገናኛ ብዙሃን አቅም መገንባት ወሳኝ የትግል ግንባሯ ይሆናል” ሲሉ ሐብታሙ ግርማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ: